*/

*/

Source

የባንክ ሂሳብ የታገደባቸው 34 የኤፈርት ድርጅቶች የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ያደረገባቸው 34 የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ ያሳገደው ሰኞ ህዳር 7፤ 2013 ለባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው። ሰላሳ አራቱ ድርጅቶቹ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ የተደረገው ከተጠረጠሩባቸው ሶስት ወንጀሎች ምርመራ ጋር በተያያዘ መሆኑን መስሪያ ቤቱ በደብዳቤው አስታውቋል። ድርጅቶች ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች መካከል “በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚፈጸሙ የዘር ተኮር ጥቃቶችን፣ የሽብር ተግባራትን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በኃይል ለመናድ ከሚሰሩ አካላት ጋር በመመሳጠርና ግንኙነት በመፍጠር በገንዘብ መደገፍ” የሚል ይገኝበታል። ድርጅቶቹ በሙስና እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎችም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ደብዳቤ ያስረዳል። የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለምርመራው ይረዳው ዘንድ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴ የሚያመለክቱ ማስረጃዎች በአስቸኳይ እንዲላክለትም ጠይቋል። የ34ቱን ድርጅቶች ሙሉ ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ

ዘገባው የEthiopia Insider ነው።

2 hours ago · Public · in

Report Page