☆☆

☆☆


#ነብዩሏህ_ዩሱፍ(ዐለይሂ ሰላም)

ክፍል 3⃣

አሁን ዩሱፍ ህዝቡ ዘንድ ልዩ ቦታ አለው።አብዝሀኛውም የሀገሪቱ ነዋሪ
የዩሱፍን ጥሪ ተቀብሏል...እንዲህ እንዲህ እያሉ 7 አመታት ካሳለፉ በኋላ
የድርቁ ዘመን ከች አለ።
ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ
ምድርም ይተሙ ጀመር።በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ
ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር
ረግጠው በማያውቁት ወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ::

በግዜው ከመንግስት መጋዘን ሁሉም እህል ሲሸምት ስሙን እና የመጣበትን
ሀገር እያስመዘገበ ነበር የሚሸምተው።እነዚህም ወንድሞቹ ስማቸውን
እስመዝግበው እህላቸውን ከመረከባቸው በፊት ዩሱፍ የከንዓን ሰዎች
መጥተዋል የሚል ወሬ ሰምቶ ሊያጣራ ሲሄድ ወንድሞቹን ተመለከታቸው።
ምንም እንኳን እሱ ቢያውቃቸውም እነሱ ግን በፍፁም ሊያውቁት
አልቻሉም።ግን ዝም ብለው በግምት፦" ይህ ፊት አዲስ አልሆነብኝም
ይባባላሉ" እርስ በርስ....
ዩሱፍም ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሰልፈኛ መሀል ለ40
አመት የተለያያቸውን ወንድሞቹን የሰሩበትን ተንኮል ወደ ጎን አድርጎ በናፍቆት
ተሸንፎ ስለማንነቱ ምንም ሳይነግራቸው ወደሚኖርበት ቤተ መንግስት ይዟቸው
ሄድ።
ይህችን ሌሊትም እሱ ጋር አሳልፈው በነጋታው እንደሚሄዱ ካሳመናቸው በኋላ
በጥሩ መስተንግዶ እራት አብልቷቸው ያዕቁብ ስለተባለው ነቢይ መጠየቅ
ጀመረ።በህይወት እንዳለ እና ዩሱፍ በተባለው ልጁ ሀዘን ምክንያት በጣሙን
እንደተጎዳ ነገሩት።ዩሱፍ ይህን ሁሉ ሲሰማ ሆድ እየባሰው ከእንባው ጋር
ትንቅንቅ ቢገጥምም ይህን ሀዘኑን ግን ለወንድሞቹ ግልፅ ሊያደርግ
አልፈለገም።ያውቁኛል ብሎ ሰግቶ.....
በነጋታው ዩሱፍ አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ለእህሉ የከፈሉትን ገንዘብ
በየከረጢታቸው ውስጥ ደብቁትና ሳያውቁ ስጧቸው" ብሎ አዘዘ። ዩሱፍ
ባዘዘውም መልኩ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ በየከረጢታቸው ተጨመረላቸው።
በመጨረሻም ሲሸኛቻው፦"በሚቀጥለው ዙር ስትመጡ ከንዓን ትታችሁት
የመጣችሁትን ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ። እሱን ካላመጣችሁት ግን
ምንም አይነት እህል አንሰፍርላችሁም" ብሎ ሸኛቸው።
እነሱም እንደሚሞክሩ ቃል ገብተውለት ጉዞ ወደ ከንዓን ጀመሩ።ረጅም
ተጉዘው ከንዓንም ሲደርሱም በግብፅ ከተማ የገጠማቸውን ሁሉ ለአባታቸው
ያዕቁብ ተረኩለት'ና በቀጣይ ዙር ግን ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያሚንን
ካላመጡ ምንም አይነት ስፍር እንደማይሰፈርላቸው ነገሩት።
አባታቸው ያዕቁብ ግን ልጆቹ ከዚህ በፊት በልጁ ዩሱፍ የፈፀሙትን በማስታወስ
ዳግም ልጁን ቢንያሚንን ለነሱ አምኖ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም
ነበር።ይሁን እንጂ ያዕቁብ ምንም እንኳን ውድ ልጁን ቢንያሚንን ከአጠገቡ
ማራቅ ቢከብደውም ከፊትለፊቱ የተደቀነው ድርቅ እና ቸነፈር ቢንያሚንን ወደ
ግብፅ ለመላክ አስገድዶታል።
ከመላኩ በፊትም ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦"ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን
(ቢንያሚንን) በእርግጥ
የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል
ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ
ጋር ፈፅሞ አልልከውም" አላቸው።
መተማመኛቸውንም ቃል ኪዳን በሰጡት ጊዜ ፦"አላህ
በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው" አላቸው።
በገቡት ቃል ኪዳን መሰረትም ቢንያሚንን ከአባታቸው እቅፍ አውጥተው
ከከንዓን ምድር ነዋሪዎች ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ከመጀመራቸው በፊትያዕቁብ
ልጆቹን ነጥሎ፦" ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን
በተለያየ በሮች ግቡ፤ ከአላህም (ፍርድ)
በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤
ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ
ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ" ብሎ መከራቸው።
በከንዓን እና በግብፅ መሀከል ያሉትን በረሃማ እና አሸዋማ መንገዶችን
ካቋረጡ በኋላ የዩሱፍን ታናሽ ወንድም ይዘው ቤተ መንግስት ገቡ።ዩሱፍም
ከመጀመርያው በተሻለ መልኩ ካስተናገዳቸው በኋላ ታናሽ ወንድሙን ለግል
አውጥቶ፦"እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት
በነበሩትም ሁሉ አትቆጭ" ብሎት ነገ እሱን ግብፅ ሊያስቀረው የንጉስ ዋንጫ
በሱ ከረጡት እንደሚሸጉጥበትም ጨምሮ ነግሮት ለአዳር ወንድሞቹ ጋ
አቀላቀለው።
ጠዋትም ለጉዞ በተዘጋጁ ግዜ ዩሱፍ እቃዎቻቸውን አስጭኖላቸው
ሸኛቸው።ብዙም ሳይርቁም ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ከአንድ ኮረብታ ላይ ሆነው፦"
እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ" በማለት
ተጣሯቸው።
እነሱም ዞረው፦" ምንድነው የጠፋችሁ?" አሉ።
ዩሱፍም፦" ፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል
ጭነት ሽልማት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ
ነኝ" አላቸው።
እነሱም፦" በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት
እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም
አልነበርንም" አሉት።
ዩሱፍም፦" ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው?" አላቸው።
እነሱም፦"ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ
የተገኘበት ሰው (ራሱን አገልጋይ አድርጎ መወሰድ) ነው፤ እርሱም
ቅጣቱ ነው። እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን" ብለው መለሱለት።
(ፍተሻውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት
በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን)
ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት።ሁሉም ደነገጡ ሚሉት ጠፋባቸው በዚህ
አጋጣሚ እራሳቸውን ለማዳን፦"እሱ ቢሰርቅ ምንም አይደንቅም አንድ ታላቅ
ወንድሙም እንዲህ ይሰርቅ ነበር" አሉ።
ዩሱፍም በውስጡ፦"እናንተ ሥራችሁ የከፋ
ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው" አለ።
ከዚያም እነሱ ራሳቸው በተስማሙት መሰረት እቃውን የሰረቀውን ቢንያሚንን
ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፦"አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ
(ለቢንያሚን) በእርግጥ ትልቅ
ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ፋንታ
አንደኛችንን ያዝ፤( ይህን ከፈፀምክ) እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ
እናይሃለንና" አሉት።
ዩሱፍም፦"ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ካገኘነው ሰው ሌላን ሰው ከመያዝ በአላህ
እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ከፈፀምን በእርግጥ በዳዮች ነን" አለ።
ዩሱፍንም ለምነው ለምነው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጎን ነጠል ብለው መመካከር
ጀመሩ።በመሀልም ታላቅ ወንድማቸው፦" አባታችሁ በናንተ ላይ
ከአላህ የሆነን መታመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ
የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ
ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ
ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ
እስከሚፈርድልኝ ድረስ የግብፅን ምድር
አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።


ክፍል 4⃣ ኢንሽአላህ
ይ........ቀ.. ....ጥ......ላ.....ል፡፡

#Share
💠💠💠💠💠💠💠💠
@Islam_firstchannel
@Islam_firstchannel
💠💠💠💠💠💠💠💠

Report Page