*/

*/

From

የፌደራል ፖሊስ በ96 ሲቪልና ወታደራዊ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን አስታወቀ
================================================= የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተፈላጊ ናቸው ባላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችንና አባላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ በ96 ግለሰቦች ላይ ማውጣቱን አስታወቀ። ፖሊስ መያዣ ትዕዛዙን ያወጣው ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል ያላቸውን ግለሰቦች አድኖ በመያዝ ለሕግ ለማቅረብ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም የእስር ማዘዣው የወጣባቸው ሲቪልና ወታደራዊ ግለሰቦች "ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያለቸውን ኃይሎች በመመልመል በትግራይ ክልል ውስጥ ስልጠናዎችን፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን" ያደረጉ ናቸው ብሏል። እንዲሁም "በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሔርን ከብሔር በማጋጨት እና በሐይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንጹሐን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን" የፌደራል ፖሊስ የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸውን ሰዎች ዝርዝር ይፋ ባደረገበት መግለጫው ላይ አመልክቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባላትን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት የሆኑ የሰላሳ ስምንት (38) ግለሰቦችን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወቃል። ዐቃቤ ሕግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የጠየቀባቸው ግለሰቦች በተለያዩ ወንጀሎች ስለተጠረጠሩ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ እነዚህም "ከፍ ያለ የአገር ክህደት በመፈጸም፣ በሕገ-መንግስቱና በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ በተደረገ ወንጀልና የጦር መሳሪያ ይዞ ማመፅ" ተጠቅሷል።

37 minutes ago · Public · in

Report Page