*/

*/

From

"የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው ይገኛል" - ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ

****************


(ኢ.ፕ.ድ)

የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው እንደሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ አረጋገጡ።

የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከምሁራን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ፅንፈኛው ሀይል በሠራዊቱ ላይ ያሴረውን ሴራ ፣ ባለፉት ሁለት አመታት የራሱን ሀይል እንዴት እንደገነባ ፣ የሀገር ክህደቱንና የፈፀማቸውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት የሰራቸውን ህዝባዊ ተግባራት አብራርተዋል ፡፡

በአሁኑ ወቅትም “ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን በሁሉም ግንባሮች ከሀዲውን ሀይል እየደመሰሰው ይገኛል” ብለዋል።

ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ እያከናወነ ያለው ህግን የማስከበር ስራ በጥንቃቄ ፣ በሰለጠነና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ በህዝብ እና በልማት ላይ ጉዳት ሳያስከትል እየፈፀመ እንደሚገኝም ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ገልጸዋል፡፡

“ የህወሓት ከሀዲ ሃይል ሠራዊታችን ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች በተለይም በማይካድራ እና በሽራሮ ባደረሰበት ሽንፈት የተነሳ ገዳይ ቡድን በመመደብ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ፣ የእርስ - በርስ ግጭት ለማስነሳት ጥሯል ነገር ግን አልተሳካለትም” ብለዋል ፡፡

የመከላከያ ሠራዊታችንን በየትኛውም ታክቲክ ሊዋጉት የሚያስችል ቁመና እንደሌላቸው የጠቆሙት ሌተናል ጄኔራል አስራት ፣ ውጊያውን የትግራይ ህዝብም አይፈልገውም ብለዋል ፡፡

ለዚህም ነጻ በወጡ አካባቢዎች የትግራይ ህዝብ ያደረገውን አቀባበል እና ድጋፍ በዋቢነት ጠቅሰዋል ፡፡

በውይይቱ የተሳተፉት ምሁራንም በግልም ሆነ በጋራ ድምፃቸውን በማሰማት ከህዝብ ጎን እንዲቆሙ መጠየቃቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Report Page