*/

*/

From

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሶስተኛውን የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 25ተኛ አመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ከንውኖች እያከበረ የሚገኝው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዛሬ ሶስተኛውን የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡

ውይይቱ “ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እና ለሀሳብ ብዝሀነት የሚዲያዎች ሚና” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ በግጭት ወቅት የሚዲያዎች ሚና ምን መምሰል እንደሚኖርበት ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የዴሞክራሲ ተቋማት የተለያየ ዘርፍ ምሁራን እና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እያከበረ የሚገኘውን 25ኛ አመት በአል አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ባለፉት 25 አመታት በሀገረ መንግስት ግንባታ የሚዲያው ሚና እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚዲያ ተደራሸነት እና ስርጭት ዙሪያ ያተኮሩ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው።

Report Page