...

...


የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሁመራ 60 ኪ.ሜ ወደ ምሥራቅ ኢድሪስ በሚባል ቦታ ላይ የሕወሓት የጥፋት ቡድንን በመደምሰስ ላይ ይገኛል- ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ!


በሕወሓት የጥፋት ቡድን ከበባ ውስጥ ገብቶ ለአምስት ቀናት ምግብና ውሃ ተከልክሎ የነበረው የሰሜን ዕዝ ጦር ከከበባ በመውጣት ራሱን መልሶ በማደራጀት እያጠቃ በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠር ወደፊት በመገስገስ ላይ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት ከሁመራ 60 ኪ.ሜ ወደ ምሥራቅ ኢድሪስ በሚባል ቦታ ላይ የጥፋት ቡድኑን እየደመሰሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል።“ሠራዊታችን በተፈጸመበት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመበሳጨቱ በከፍተኛ ወኔ፣ ጀግንነትና ተነሳሽነትም ሁሉንም ነገር ወደነበረበት ለመመለስ እና ከሃዲውን ቡድን በሕግ ፊት ቀርቦ እንዲቀጣ ለማድረግ እየሠራ ነው” ብለዋል-ጀኔራል ብርሃኑ።


በጥፋት ቡድኑ ከበባ ውስጥ ገብቶ የነበረው 7ኛ ሜካናይዝድ፣ 8ኛ ሜካናይዝድ፣ 23ኛ ክፍለ ጦር፣ 11ኛ ክፍለ ጦር፣ 31ኛ ክፍለ ጦር፣ 20ኛ ክፍለ ጦር፣ 4ኛ ሜካናይዝድ፣ 5ኛ ሜካናይዝድ በሙሉ የሰሜን እዝ ሠራዊት እንደነበረ ለኢዜአ ገልጸዋል።

“ይህ ሠራዊት ለአራት እና አምስት ቀናት ምግብ እና ውኃ ተከልክሎ፣ ራሱን በውኃ ጥም ውስጥ ሆኖ በጽናት የተከላከለ ጀግና እና የመከላከያ ሠራዊት ሞዴል ሆኖ በመገኘቱ በራሴና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ” ብለዋል።

የሠራዊቱ ጀግንነትም ሲዘከር የሚኖር ገድል መሆኑን አስገንዝበው፣ “እውነተኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠራዊት መሆናችሁን በተጨባጭ ስላስመሰከራችሁም ከፍተኛ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ” በማለት ተናግረዋል።


ሠራዊቱን ከከበባ ለማላቀቅ ከምሥራቅ፣ ከደቡብ እና ከምዕራብ ፈጥነው በመድረስ የሰሜን እዝን ለመታደግ ለቻሉት የሠራዊቱ አመራር እና አባላት የ“እንኳን ደስ ያላችሁ” መልእክት አስተላልፈዋል።ከዚህ በኋላ ቀሪው የሠራዊቱ ተልእኮ እስካሁን ከተፈጸመው ተግባር አንጻር አነስተኛ መሆኑን የጠቆሙት ጀኔራል ብርሃኑ፤ ሠራዊቱ ይህንን በመረዳት ቀሪውን ተልዕኮ በአጭር ጊዜ እንደሚወጣ ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።ሠራዊቱ ከከበባ በመውጣት እና ራሱን መልሶ በማደራጀት ባለፉት ሁለት እና ሦስት ቀናት ከዳንሻ ጀምሮ ሁመራ በሚገኘው ትርካን አየር ማረፊያ እንዲሁም ባዕከርን በማጥቃት እና በመቆጣጠር 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦርን ከከበባ ማላቀቁን ተናግረዋል።


ከከበባ ከተላቀቀው 5ኛ ሜካናይዝድ ጋር በመሆንም ሁመራን ነፃ በማውጣት ሉግዲ፣ ማይካድራንና በረከትን ነፃ እንዳወጣ አመልክተዋል።ሠራዊቱ የትግራይን ሕዝብ እና የትግራይን የፀጥታ ሃይል ጭምር ነፃ ለማውጣት ግስጋሴውን ወደ ሽሬ መቀጠሉን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጠቁመዋል።“ሕገ ወጡ ጁንታ ሕዝቡ እና የፀጥታ ኃይሉን እንደ ምሽግ ስለተጠቀመ፣ ሕዝቡንና የፀጥታ ሀይሉን ከዚሁ ወንጀለኛ ቡድን በመነጠል እና እሱኑ ዒላማ ያደረገ እንቅስቃሴ እየተካሄደም ይገኛል” ያሉት ጀኔራል ብርሃኑ፣ ሕግ የማስከበሩን ሥራ ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁለንተናዊ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አመልክተዋል።የመከላከያ ሠራዊት ጁንታውን ለሕግ ለማቅረብ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሕዝቡ እንዳይጎዳ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ለጦርነት ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ላይ እያለ በሕወሓት የጥፋት ቡድን ልዩ ኃይል አማካኝነት ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንኑ ተከትሎ መንግሥት ሕግ የማስከበር እና የህልውና ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


@YeneTube @FikerAssefa

Report Page