*/

*/

From

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ህዝብ የትህነግ ጁንታን ህግና ስርዓት ለማስከበር ለተሰለፉት የሐገር መከላከያና የአማራ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት የሚውል 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የዕለት ምግብ ድጋፍ አደረገ።

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) መከላከያ ሰራዊቱ የሃገር ዳር ድንበር እያስከበረ የትግራይን ህዝብ በልማት እየደገፈ የኖረ የአብራክ ክፋያችን ሆኖ ሳለ የዘራፊው ቡድን ጥቃት መፈጸሙ አሳዝኖናል ብለዋል የብሔረሰብ አስተዳደሩ የሃገር ሽማግሌዎች፡፡

የሃገር ሽማግሌዎች መንግስት በአጥፊ ቡድኑ ህወሃት ላይ እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር ርምጃም እንደግፋለንም ብለዋል።

የኢትዮጵያን ህዝብ በብሔር በመከፋፈል ዜጎች በማንነታቸው ጥቃትና እንግልት እንዲደርስባቸው ህገወጡ ትህነግ ከኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት ጥፋት ሲፈፅም ቆይቷል፤ ከሰሞኑም በመከላከያ ኃይላችን ላይ የፈጸመው ጥቃት እብሪተኛነቱን ያረገገጠ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የከሃዲውን ቡድን ጥቃት በመመከት ህግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያደርገው ጥረት የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እስከ ጦር ግንባር ለመሰለፍ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አህመድ ሐሰን እንዳሉት ከሃዲው የትህነግ ህገወጥ ቡድን የሃገር መከታ በሆነውና የትግራይን ህዝብ ከ20 ዓመታት በላይ ሰላሙን በመጠበቅና ልማቱን እያገዘ ባለው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረሱ ከተሰማበት ዕለት ጀምሮ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም ቁርጠኝነቱን እያሳዬ ነው።

ህዝቡም ለሰራዊት የኋላ ደጀንነቱን ለማረጋገጥ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የዕለት ምግብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ህገወጡ ትህነግ ከኦነግ ሸኔ ጋር በመተባበር ዜጎች በማንነታቸው ጥቃትና እንግልት እንዲደርስባቸው አድርገዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የኢትዮጵያ ህዝብም የትህነግን ጽንፈኛ የትግል አካሄድ በመገንዘብ ከመከላከያ ኃይልና ከአማራ ልዩ ኃይል ጎን መሰለፍ እንዳለበትም አሳስበዋል።

የመከላከያ ኃይልና የአማራ ልዩ ኃይል የትህነግ ከሃዲ ቡድን ላይ እያደረጉት ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በመደገፍ ህዝቡ የተለያዩ የምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል።

ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ

Report Page