*/

*/

From

ዶ/ር ደብረጺዮን ጦርነት ቆሞ ድርድር እንዲካሄድ መጠየቃቸው ተሰማ
===================================== የፌደራል መንግሥት ከአማራ ክልል ጋር በመሆን ከትግራይ ክልል ኃይሎች ጋር ወደ ግልጽ ጦርነት ከገቡት ስድስት ቀናት አልፈዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት አዳዲስ ነገሮች ተሰምተዋል። ከእነዚህም መካከል የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጸዮን (ዶ/ር) ድርድር እንዲካሄድ መጠየቃቸው አንዱ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ቢያንስ በ8 ቦታዎች ጦርነቶች እየተካሄዱ ይገኛል ብሏል። የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲካሄድ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ደብረጺዮን (ዶ/ር) የአፍሪካ ሕብረት በፌደራል እና ትግራይ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ጦርነቱን እንዲያስቆም እና ከእርስ በእርስ ጦርነት አገሪቷን እንዲታደግ ጠይቀዋል። የክልሉ ፕሬዝደንት ለወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት በጻፉት ደብዳቤ ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ደብረጺዮን (ዶ/ር) በደብዳቤያቸው "ፖለቲካዊ ችግሮች በወታደራዊ አማራጮች እንደማይፈቱ ጽኑ እምነት አለኝ" ብለዋል። በተመሳሳይ ሮይተርስ የዜና ወኪል ደብረጺዮን (ዶ/ር) ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲደረግ መጠየቃቸውን ትናንት ምሽት አስነብቧል። ይህ ይሁን እንጂ በፌደራል መንግሥቱ በኩል ለድርድር ፍላጎት ያለ አይመስልም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ትናንት ለውጪ ማህብረሰቡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር መንግሥት የጀመረውን እርምጃ ያጠናቅቃል ብለዋል። ከሁለት ቀናት በፊትም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በትዊተር ገጻቸው ላይም "ወንጀለኛ አካላት ዕርቅ እና ድርድር ፈላጊ በመምሰል ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ አይችሉም። የሚከናወነው ኦፕሬሽን ዓላማው፣ የሚገባቸውን ቅጣት ሳያገኙ ከገደብ አልፈው የቆዩትን አጥፊ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሀገራችን ሕግጋት መሠረት ተጠያቂ ማድረግ ነው" ብለው ነበር።

Yesterday at 11:01 PM · Public · in

Report Page