*/

*/

From

ህወሃት ከተወገደ ህዝቡ ሰላሙንና ነጻነቱን ያገኛል - የትግራይ ተወላጆች
******************* (ኢፕድ)

ህወሃት ከተወገደ የትግራይ ህዝብ ሰላሙንና ነጻነቱን ያገኛል ሲሉ የትግራይ ተወላጅ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ገለጹ።

በከሃዲው የህወሓት ቡድን ላይ እየተወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንደሚደግፉም ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ተወላጅ አባላት፣ ደጋፊዎችና ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ህወሓት የሀገር አለኝታና መከታ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።

“ድርጊቱ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ባህልና እሴት አፈንግጦ ብቻውን በአምባገነናዊነት የሚኖር ቡድን ለመሆኑ ማሳያ ነው” ብለዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ሃሳባቸውን የሰጡት የትግራይ ተወላጆቹ እንዳሉት፤ የትግራይ ህዝብን የማይወክለው ህወሓት ከተወገደ የትግራይ ህዝብ ሠላሙንና ነጻነቱን ያረጋግጣል፡፡

የህወሓት ቡድን መሪዎች ተይዘው ለሕግ ቀርበው የህግ የበላይነት ምን እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ለወሰደው እርምጃና ዕድሜውን ሙሉ ሲሰራ ለነበረው ጥፋት ተግባር የእጁን ማግኘት እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በዚህ ቡድን ላይ እርምጃ በሚወሰድበት ወቅትም ህዝቡን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ህወሓት የክፋት መገለጫ መሆኑን ገልጸው፤ እየተወሰደበት ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በወንጀለኛው በህወሓት ቡድን ላይ ነው፡፡

የህወሃት ክህደት አላግባብ ለመበልጸግ ከማሰብና ስልጣንን የሙጥኝ ከማለት የመነጨ እንደሆነ ተናግረዋል።

ቡድኑ ወደ ሰላማዊ መስመር እንዲገባ በተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም ሰላማዊ አማራጭን መጠቀም አለመፈለጉን በተግባር እንዳሳየ ገልጸዋል።

በቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ሕገ ወጥ ቡድኑን ለሕግ ማቅረብ ዓላማ ያደረገ እንደሆነም አብራርተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Report Page