*/

*/

From

ክፍተቱ እንዴት ተፈጠረ? ተጠያቂውስ ማን ይሆን ?

በትናንትናው የአማራ ብሔር ተወላጆች ጥቃት ዙሪያ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ የኢቲቪ ዜና አንባቢ " ጥቃቱን አስቀድሞ መከላከል ያልተቻለው ለምንድነው?" በማለት ለጠየቀው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ ቃል በቃል እንደሚከተለው ላስቀምጥ፦

"ችግሩ የተፈጠረው መከላከያ እዚያ አካባቢ ነበር፣ መከላከያ ሲወጣ የኛ የፀጥታ ኃይል በወቅቱ ቶሎ አለመድረስ ነው። የሰዓታት ጋፖች አሉ፣ ስለዚህ አካባቢው የደረሱት ደግሞ ትንሽ ከተማ የወረዳ ከተማ ነው የደረሰው። አሁን ይኼ ድርጊት የተፈፀመው ከወረዳ ዋና ከተማ 85 ኪ.ሜ. የምትርቅ የገጠር ቀበሌ ነች፣ እና ድንበር ላይ ያለች ገጠር ነች ፣ በአብዛኛው የአማራ ብሔረሰብ ድሮ በደርግ ጊዜ ከወሎ አካበቢ ተፈናቅለው እዚያ የሰፈሩ ሕብረተሰብ አካባቢ ነው ሆን ተብሎ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚደረግ ስለሆነ ያቺ ቦታ ተመርጣ ኃይል ሳይደርስ ማታ 12 ሰዓት አካባቢ ነው ሄዶ ይህን እርምጃ የወሰደው.."

ጥያቄዎቹ አሉኝ፦

1. መከላከያ የዜጎች ደህንነት ስጋት ያለበትን አካባቢ ለቅቆ የሚወጣው መቼ ነው? በእኔ እምነት በአካባቢው ሰላም ሰፍኖ ዜጎች እንዳሻቸው መንቀሳቀስ ሲጀምሩ መሰለኝ። የተሰጠውን ግዳጅ በብቃትና በአስተማማኝ ደረጃ ሲወጣው መሰለኝ። አሁን በገሃድ እንደታየው ከሆነ መከላከያ ጥቃት የደረሰበትን አካባቢ ለቅቆ የወጣው የሕዝቡ ሰላም ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ነበር። ምክንያቱም ጥቃቱ በሰዓታት ውስጥ መፈፀሙ ጥቃት አድራሾቹ ወትሮም እዚያው በመከላከያ አፍንጫቸው ሥር ነበሩ ማለት ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው መከላከያ ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት በተጨማሪ የራሱ የሆነ የደህንነት መረብ እንዳለው ይነገራል። የአካባቢው ሕዝብ መከላከያ አካባቢውን ለቅቆ እንዳይወጣ መማፀኑ ከመከላከያ ደህንነት የመረጃ መረብ ይልቅ ሕዝቡ ዘንድ የተሻለ መረጃ ስለመኖሩ ጥቆማውን እየሰጠን ይሆን?

2. መከላከያ የደህንነት ስጋት እንዳለ የሚገመተውን አካባቢ ሲለቅ እንዴት መልቀቅ አለበት የሚለው ሁለተኛ ጥያቄዬ ነው። አሁን በኮሚሽነሩ እንደተነገረን መከላከያ አካባቢውን የለቀቀው ለክልሉ ልዩ ኃይል ሳያስረክብ ክፍተት ፈጥሮ (የሰዓታት ጋፖች የተበላው) ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሚሊተሪ ሳይንስና የደህንነት ኤክስፐርት መሆን የሚጠበቅብን አይመስለኝም። በእኔ አረዳድ መከላከያ አካባቢውን መልቀቅ ያለበት ክፍተት ፈጥሮ ሳይሆን ምንም ክፍተት ሳይፈጠር እዚያው ሆኖና አስቀድሞ ለአካባቢው ፀጥታ ኃይል ካስረከበ በኋላ ነው። አሁን ግን ኮሚሽነሩ በርክክቡ ሂደት ክፍተት ተፈጥሯል እያሉን ነው፣ እንዲሁም ችግሩ የተፈጠረው የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው "በወቅቱ በቶሎ" ባለመድረሱ ነው ብለውናል።

3. ይህ "ክፍተት" እና "በወቅቱ በቶሎ አለመድረስ" የሚለው ገለፃ ለሴራ ፖለቲካ ትንተና በእጅጉ የተጋለጠ ነው። ታዲያ አንዳንዶች ከዚህ ተነስተው መንግስት ተቃዋሚዎችን ማኖ እያስነካ ከመጪው ምርጫ ለመግፋት ሆን ብሎ የከፈተው "ክፍተት" ነው በማለት ቢተነትኑ ለምን ይፈረድባቸዋል? ነገሩ እውነት ከሆነ ደግሞ አንዳንድ የፖለቲካ "game" ነጥሮ ወደ ራስ ነው የሚመለሰው..ሳይጠበቅ "Rebounce" አድርጎ ያልተጠበቀ ውጤት ያመጣል። የብልፅግና ፓርቲ በትናንትናውና ከዚያም በፊት የተወሰዱ የጥቃት እርምጃዎችን ተከትሎ ደጋፊዎቹ በየፌርማታው እየተንጠባጠቡ እያለቁበት እንደሆነ አናሊስስ እየሰራ ይሆን? በአሁኑ ወቅት ጭፍን የብልፅግና ደጋፊዎች ሳይቀሩ ወደ አክራሪ ተቃውሞው ካምፕ እየገቡ ነው።

4. በመጨረሻም ለተፈጠረው "ክፍተት" የሚጠየቅ አካል የለም?

Report Page