*/

*/

From

▶️➖ኮሎምቦስ እና የጨረቃን ግርዶሽ➖◀️
============================
🌖 የጨረቃ ግርዶሽ በምድራችን ወቅት ጠብቆ ይከሰታል።። የዚህ ክስተት ዋነኛው መንስኤ ምድራችን በፀሃይና ጨረቃ ማካከል ስትገባ ከፀሃይ ተቀብላ የምታንፀባርቀው ብርሃን ጨረቃ በሙሉው ስለማይደርሳት ነው። ምድር ጨረቃን ትጋርዳለች ማለት ነው። ምድራችን ከባቢ አየር ባይኖራት ኖሮ በዚህን ወቅት ጨረቃ ሙሉ ለሙሉ ላትታይም ትችላለች። ምክንያቱም የመሬት ጥላ ሙሉ ለሙሉ ጨረቃ ላይ ስለሚያርፍ (በአምብራ ክልል)። ነገር ግን ምድራችን ከባቢ አየር 50 ማይል ከመሬት ክፍ ብሎ በምድር ዙሪያ ቀለበት ስለሚሰራ ይህ ከባቢ አየር ከፀሃይ የሚነሳዉን ነጭ ብርሃን ውስጥ የሚገኙትን ህብረ-ቀለማት አስቀርቶ ቀዩን ብቻ ሲያስተላልፍ ይህ ቀይ የብርሃን ቀለም ጨረቃ ላይ ሲያርፍ ደም መስላ ተታያለች።

🌖 ኮሎምቦስ አዲስ አለም ፍለጋ ወደ አሜሪካ በመጣበት ዘመን የጨረቃ ግርዶሽ ከሞት አድኖታል። ኮሎምቦስ ከነግብረ-አበሮቹ ለስድስት ወር ከቀድሞዎቹ የአሜሪካ የምድር ባለቤቶች ሲረዳ ከቆየ በኋላ የእርሱ ሰዎች ነዋሪዎቹን ዘርፈው ሲገድሉ ነዋሪዎቹም ተናደው በኮሎምቦስ እና ሰዎቹ ላይ ይነሳሉ። ለኮሎምቦስ አንድ ሃሳብ መጣለት። በጀመን የውቅቱ ህዋ ተመራማሪዎች የተዘጋጀ የጨረቃ ግርዶሽ አልማናክ መተንበያው መጽሐፍ በእጁ ነበር እና ከሶስት ቀን በኃላ የጨረቃ ግርዶሽ እንደሚኖር ተረዳ። ስለዚህ ኮሎምቦስ የጎሳ መሪዎቹን አስጠርቶ እኔ የማመልከው አማልክት በእናንተ ተቆጥቷ ምልክቱም ከሶስት ቀን በኋላ ጨረቃን ወደ ደም ይለውጣል ይላቸዋል። እነርሱም ሶስቱን ቀን በተጠንቀቅ ጠብቀው እርሱ እንዳለው ክስተቱ ተከሰተ። በወቅቱ የጨረቃን ግርዶሽ ሊተነበይ ይቻላል የሚል እውቀቱን ስላልነበራቸው። እነርሱም ፈርተም ታዘዟቸው። ማሳደዱንም ተዉት። አሁንም ቢሆን ሳይንስ የጨረቃን ግርዶሽ የወደፊቱን የብዙ ዘመን መተንበይ ይችላል። ይህንን የ NASA ሊንክ ቢመለከቱ እስከ 2050 ያለው የጨረቃን ግርዶሽ ተዘርዝሯል።

ማንም ተነስቶ የፀሃይን ግርዶሽ በባህላዊ መንገድ ተነበይኩ ቢል ይቀልዳል።🤣🤣🤣

Report Page