..

..

Think Abyssinia
Think Abyssinia

 ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ስውያሜውን ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ቀየረ።

ፓርቲው ስያሜውን የቀየረው በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ባለው 12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ደርጅቱ የአርማ ለውጥም ማድረጉንብም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት አርማው መደቡ ከላይ አረንጓዴ መሃል ላይ ጎህ ሲቀድ የሚኖር ቀለም (ቢጫ) ሆኖ ከግርጌ ቀይ እንዲሆን ተወስኗል።

እንዲሁም መሃሉ ላይ የስንዴ ዘለላ እና የኢንዱስትሪ ምልክት በግራ እና በቀኝ እንዲሆን የአባይ ወንዝ እና መጽሃፍም በአርማው መሃል ላይ እንዲካተት ተወስኗል።

ድርጅታዊ ጉባዔው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም ከፓርቲው የሚሰናበቱ አባላት ልየታ እየተካሄደ ይገኛል።

@ThinkAbyssinia

Report Page