..

..

🦁Think አቢሲኒያ 🦁
🦁Think Wise Think Abyssinia 🦁

፨ሜቄዶናውያን የሀገሪቱን መጠሪያ ለመቀየር የቀረበው ሀሳብ ላይ ድምጽ እየሰጡ ነው!!

•የሀገሪቱ ህዝብ እየሰጠ ያለው የህዝበ ውሳኔ ድምፅ የሜቄዶኒያ መጠሪያ ወደ ሰሜን ሜቄዶኒያ ይቀየር ወይስ ባለበት ይቀጠል የሚለው ላይ ነው።

•የስያሜው መቀየር በተለይም ለረጅም ዓመታት ከግሪክ ጋር በመጠሪያ ምክንያት የነበረችበትን እሰጣ ገባ ያስቀራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

•እንዲሁም ሜቄዶኒያ የአውሮፓ ህብረት እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ናቶ’ን እንድትቀላቀለም ይረዳታል ተብሏል።

•1 ነጥብ 8 ሚሊየን ህዝብ ይሳተፍበታል ለተባለው የህዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥም ዛሬ ጠዋት ነው የምርጫ ጣቢያዎች ክፈት የተደረጉት።

•በህዝበ ውሳኔው መሰረት አብዛኛው ድምጽ ስያሜው እንዲቀየር የሚስማማ ከሆነ የሀገሪቱ ፓርላማ ሜቄዶኒያ የሚለውን መጠሪያ ወደ ሰሜን ሜቄዶኒያ የመቀየር ስልጣን ያገኛል ተብሏል።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com


🦁• @ThinkAbyssinia •🦁

Report Page