*/

*/

From

የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማስቀጠያ ቅድመ ዝግጅትና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት የግምገማ መድረክና አውደ ርዕይ ከነገ ጀምሮ በጅማ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ይካሄዳል።
===============================================

በምክክር መድረኩ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የሀገሪቱ 44 መንግስታዊ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ይሳተፋሉ።

የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ እንዲሁም የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበባየሁ ቶራ በምክክር መድረኩና አውደ-ርዕዩ ለመሳተፍ ወደ አባ ጅፋር ሀገር ጅማ ገብተዋል።

ይህ የምክክር መድረክና አውደ-ርዕይ ከነገ ጀምሮ ለሶስት (03) ተቀታታይ ቀናት እንደሚቆይና የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችም ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ዩኒቨርሲቲያችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት ለአውደ-ርዕዩ ተሳታፊዎች ይቀርባሉ።

Higher Education and Training Continuation Preparation and Covide-19 Outbreak Response Performance Review Forum and Exhibition organized by Jimma University starts tomorrow.
==========================================

The forum will be attended by 44 government institutions of Higher Education, including Wolayita Sodo University.

The President of our University, Prof. Takele Tadesse, the Vice President for Research and Community Service, Dr. Mesfin Bibiso, and the Vice President for Administration and Student Services, Dr. Abebayehu Tora, arrived in Jimma to participate in the forum.

This forum and exhibition is expected to last for three consecutive days starting from tomorrow and various research papers will be presented and discussed.

The activities of our university in preventing and controlling the CVD-19 pandemic will be presented to the participants.

Report Page