...

...


በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያዘዋወረ፣ በዝውውሩ የተሳተፈና ለአዘዋዋሪዎች ሽፋን የሰጠ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።


ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑ በአገሪቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወር ገንዘብ የመኖሩ አንድ ማሳያ ነው።በመሆኑም በዚሁ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተግባር ላይ ተሳታፊ የሆነ ማንኛውም አካል በወንጀል ሕግ ከመጠየቅ እንደማይድንም ጠቅላይ አቃቤ ግህ ጠቁሟል።በኢትዮጵያ በ1996 ዓም በወጣው የወንጀል ሕግ መሰረት በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፎ የተገኝ ማንኛውም አካል እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።


በጠቅላይ አቃቢ ሕግ የታክስ ወንጀሎች ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታዬ አባተ ለኢዜአ እንዳሉት በወንጀል ሕጉ መሰረት በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ አጥብቆ የተከለከለ ነው።በዋናነትም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 346 በተቀመጠው መሰረት በወርቅ፣ በጥሬ ገንዘብ እና በውጭ አገር ገንዘብ በሕገ-ወጥ መንገድ መንገድ መገበያየት የተከለከለ መሆኑን ይደነግጋል።ሕጉ ገንዘብን ከሚያዘዋውሩ ዋና ተዋናዬች ባሻገር ከነዚሁ አካላት ጋር ትብብር የሚያደርጉና ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦችንም ጭምር እንደሚያስቀጣ ነው አቶ ፋንታዩ የተናገሩት።በአሁኑ ወቅት በብሔራዊ ባንክ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ማንኛውም አካል ከባንክ ውጭ ሊያንቀሳቀስ የሚችለው እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው።


ይሕ ደግሞ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል፣ ሙስናን ለማስቀረት፣ የሕ-ወጥ የጦር መሳሪያ ግዥን ለመቀነስና ለማስቀረት እንደሚያስችል ጠቁመዋል።መንግስት በአሁኑ ወቅት የገንዘብ ቅያሬ ማድረጉም በሕገ-ወጥ መንገድ በሰዎች እጅ ላይ የሚገኝ ገንዘብን ለማምከንና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ያስችለዋል ነው ያሉት።ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በተደራጀና ውስብስብ በሆነ መንገድ የሚፈፀም በመሆኑ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል አካላት ወንጀሉን ለመከላከል ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።ሕጉ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወር ገንዘብም እንዲወረስ ያዛል ያሉት አቶ ፋንታዩ ከዚህ ባሻገርም እስከ 200 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልም ጠቁመዋል።


[ኢዜአ]

@YeneTube @FikerAssefa

Report Page