*/

*/

From

ከደቂቃዎች በፊት የአብኑ ዩሱፍ ኢብራሂም መረራ (ፕ/ር) ላይ ሲሸልል አየሁ። የተውኩትን ነገር እንዳደርግ ጋበዘኝ።

በቅድሚያ፣ በታሪክ ጉዳይ የሚነታረኩ ልሂቃን፣ በዋናነት እውነትን ለመከላለል የቆሙ አይደሉም። ተግባራቸው ይወክለናል የሚሉትን አካል በፈጀው ሁሉ መከላከል ነው። ምንሊክ የሸዋ ንጉሥ እያሉ፣ allegiance'ያቸው በሀገረ-መንግስቱ እና በሸዋ መካከል ሲዋልል እናያለን። የአፄ ዮሐንስን ወደ ደቡብ መገስገስ ተከትሎ በደነገጉት አዋጅ "የጋ*ን ከብት መዝረፍ ገታ አድርገን ሀገራችንን ከጠላት እንከላከል" ሲሉ ህዝባቸውን ተማፅነዋል [ቃል በቃል አይደለም]። (1) ኦሮሞን መዝረፍ ከስብስቴ ጀምሮ የተለመደ ነገር ነበር። በአያታቸው ንጉሥ ሳህለሥላሴ ጊዜ ደግሞ ብሶ በአመት ሁለቴ የሚከወን ተለምዶ ሆኖ ነበር። (2) ለመሆኑ ከከብት ዘራፊ እና ነፍጠኛ ያነሰ ውድመት የሚያስከትለው የቱ ነው። በውግንና ለሚደግፉ ሀይሎች "ዘራፊ ነበሩ" ከሚባሉ "ነፍጠኛ" ነበሩ የሚለውን ቢመርጡ የሚሻላቸው መስሎ ይሰማኛል። ቢያንስ "ሀገር ለማቅናት"፣ "ታላቅ ሀገር ለመመስረት" የሚሉ ሰበቦችን ሊያሰጣቸው ይችላልና። (3) የአንድነቱ ልሂቅ በሰሜን ኢትዮጵያ ስለመጡ ወራሪዎች ተናግሮ አይጠግብም። ነገር ግን ሀረሪ በግብፆች መተዳደሯን የታሪክ አጀንዳ ሲያደርጉ አናይም። አፄ ምንሊክ እንኳ ለንግስት ቪክቶሪያ በፃፉት ደብዳቤ "የኔ ችግር የቱርኮች [ግብፆች] ግረቤቴ መገኘት ነው" [ቃል በቃል አይደለም] እንጂ "ግዛቴን መውረራቸው ነው" አላሉም። ለምን እንደሆነ ቢያን መገመት የሚቻል ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ ወይም የሸዋ ነገስታት ለዘረፋ የደረሱባቸውን ወይም ውሎ-ገባ የረገጡትን ሁሉ ጥንታዊ የሀገሪቱ ሉአላዊ 'ግዛት' ማድረግ ተራ ውግንና ነው። ለነገሩ አንድ ነገር ማወቅ ይህን ለመረዳት ይጠቅማል። ለምሳሌ በአመዛኙ የአንድነቱ ሀይል የወጣበት አማራ "territorial" ህዝብ ነው። በውስጡ ያለው ማንም ይሁን ማን አያስጨንቀውም። ዋናው ነገር ድንበር መጠቅለል ነው። ለዚህ ነው ልሂቁ ሁሉን ነገር "ርስቴ" በሚል define የሚያደርገው። (ኦሮሞ ደግሞ lineage የበለጠ ይስበዋል። ከጎሳ ይልቅ territory compromise የሚደረግ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ የያዘው ድርጊታዊ ቦታ የዚህ ውጤት ነው።)

በሌላ በኩል፣ የአንድነት ሀይሉ የሚቆምለት ገዥ መደብ፣ state abuse የማድረግ luggage አለበት እያልን ነው። ሌላው ወገን በተፈጥሮው ከዚህ የነፃ ነው ማለት ሳይሆን ይህን የመፈፀም/ላለመፈፀም እድሉ አልተፈጠረለትም እያልን ነው። ሆኖም፣ ከቀደመው ተረክ ያልወጣው ልሂቅ እድሉን ለብቻው የተገባው አድርጎ ስለሚመለከት (at least unconsciously)፣ "abuse አደረግሁ አላደረግሁ ምን ቤት ናችሁ?" የሚል ቃና ይታይበታል። (እዚህ ላይ የኦሮሞን ልሂቅ የ "raison deter"- reason of the state ድህነት ሳልጠቅስ ማለፍ አይቻለኝም።)

ወደገደለው ልመለስ፣ የኦሮሞ እና የደቡብ ህዝቦች double ጭቆና ነበረባቸው እንላለን። አማራስ?! የአማራ ገበሬ በመደቡ ጭቆናን ከሁሉም የኢትዮጵያ ብ/ብ/እና ህ ገበሬዎች ጋር ይጋራል። የባህል እና ቋንቋ ተጋሮቱ ግን ኢትዮጵያ ብ/ብ እና ህ ጋር ሳይሆን ከገዥው መደብ ጋር ነበር። ከገዥው መደብ ጋር ቢያንስ አንድ የሚያስተካክለው ነገር አለ፣ ባህል-ቋንቋ። (አውሮፓ በተቃራኒው ነው። ገዥው መደብ በኢኮኖሚም ሆነ በባህል ከታችኛው መደብ ይለያል።)

እኛ መረዳት ያለብን ጉዳይ ከዚህ ቀጥሎ ይመጣል። በዋናነት የአማራ ልሂቅ የሚወክለው የአንድነት ሀይል ደርግ+ኢህአዴግ ሁለት ነገር አሳጥተውታል። ደርግ ከኔ ወገን ነው የሚለውን ስርአት ቀበረበት። ኢህአዴግ ደግሞ ቀሪ መፅናኛው የሆነውን የታሪክ ትርክት ከንቱነት አጎላ። ይህ ሀይል ከታሪካዊው የገዥ መደብ የክብር ተጋሪነት ወርዶ ከብሄር ብሄረሰቦች እንደአንዱ ሁን ሲባል እልል እያለ የሚቀበል ይመስላችኋል? ኦሮሞን "የማንነት መብትህን አውቄልሀለው" ብሎ ለተወሰኑ አመታት ማስደሰት ይቻል ይሆናል። ሆኗልም። የአማራ ልሂቅ የሚበዛበትን የአንድነት ሀይሉንስ በምን ልታግባባው ነው? ከፍ ያለውን ቦታ የሚይዘው መልስ፣ ከገዥው መደብ ጋር ይጋራ የነበረ "imaginary" የነበረውን 'ክብር'፣ ልማት actually ልተካው በተገባ ነበር። እንደየትኛውም ብሄር አፈር ገፊ፣ የድህነት መከራውን መታገሱ ሳያንስ አንድ መፅናኛው የነበረውን ታሪካዊ ሀቲት መንጠቅ በምን justify ሊደረግ ነው?! የተሸከመውን የድህነት እና ኋላ ቀርነት መከራ እስካልቀየርክለት ድረስ

ኢህአዴግ ትንሽዬ ልማት በማረጋገጥ፣ የፈነጠቀውን የመለወጥ ተስፋ፣ በዋናነት በራሱ ስህተት ሲያጨልም፣ ይህ ልሂቅ ከሁለት ያጣ ሆኖ የሚቆይበት ምክንያት አይታየውም። ቢያንስ የክብሬ መገለጫ ነው የሚለውን ታሪክ at any cost ይከላከላል።

ይህን የሚሽረው (1) የማንነት ጥያቄ (primary and secondary (2) የልማት ጥያቄ (basic ones) እና (3) መልማት ዘራሽ ጥያቄዎች (secondary) በሚፈጥሩት synthesis ነው።

Report Page