...

...


ፋሲል ከነማ በበዛብህ መለዮ ብቸኛ ግብ እዛምን እሸነፈ


በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር በሜዳው እዛምን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በመጀመርያ እጋማሽ በበዛብህ መለዮ እማካኝነት በተቆጠረች ግብ እሸንፈዋል።

በባለሜዳው ፋሲል ደጋፊዎች ደማቅ የሞዛይክ ትርኢት ታጅቦ በተካሄደው የመጀመርያ እጋማሽ የፋሲሎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ እና ሙከራ የታየበት ነበር።በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች እፄዎቹ ከሁለቱም መስመር በሚነሱ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም እንደ ያዙት የኳስ ብልጫ ሊሆን እልቻለም። ናይጀርያዊው ኢዙ እዙካ ከግራ መስመር ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ሰብሮ በመግባት ለሙጂብ እቀብሎት በእዛም ተከላካዮች በተመለሰ ኳስ እድሎችን መፍጠር የጀመሩት ፋሲሎች በተደጋጋሚ የእዛም ፍፁም ቅጣት ሳጥን ውስጥ ቢደርሱም የጠሩ እድሎችን መፍጠር ተስኖባቸው ታይቷል።የፋሲሎች ሊጠሩ ሚችሉ ሙከራዎችን ከቆሙ ኳሶች በተሻለ ሁኔታ ፈጥረዋል የዚህ ማሳያ ሚሆኑት በ6ኛው ደቂቃ ቀኝ መስመር ላይ የተገኝውን ቅጣት ምት ሱራፋኤል ዳኛቸው እሻምቶት በእዛም ተካላካዮች ተመልሶ የተገኘውን ኳስ ቅርብ የነበረው ሙጂብ ቢመታውም የግቡ የጎን መርበብ ገጭቶ ወጥቷል።በተመሳሳይ ሱራፌል ዳኛቸው ከፋሲል ሜዳ ቀኝ መስመር በረጅሙ የላከው ኳስ እጥቂው ሙጂብ ቃሲም የተከላካዩና የበረኛው አለመግባባት በመጠቀም ያገኘውን ኳስ በጨረፍታ መትቶት ለትንሽ ወደ ውጭ ሊወጣ ችሏል።እንግዶቹ እዛም በበኩላቸው በ3-5-2 እሰላለፍ ወደ ኃላ ማፈግፈግ ምርጫቸውን በማድረግ ከመስመር በሚነሱ የመልሶ ማጥቃት ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም ሚካኤል ሳማኬን እና ተቀይሮ የገባውን ጀማል ጣሰውን ሚፈትኑ እልነበሩም።


መስመር ላይ ትኩረት ያደረገው የፋሲል እጨዋወት መደበኛው የመጀመርያ 45 ተጠናቆ ዳኛው በጨመረው 2 ደቂቃዎች ላይ ፍሬ ማፍራት ችሏል።ሽመክት ጉግሳ ከግራ መስመር ያሻማው ኳስ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን በቀኝ በኩል የነበረው ሙጂብ ወደ ውስጥ የመለስው ኳስ በዛብህ መለዮ በጥሩ እጨራረስ አፄወቹን በመሪነት ወደ ዕረፍት እንዲወጡ እድርጓል።

በሁለተኛው እጋማሽ ተሽለው የቀረቡት እዛሞች እሁንም መስመር ላይ ትኩረት እድርገው እድሌችን ፈጥረዋል።በተለይ ፊት ላይ የነበረው እብርይ ቼርሞ ና ኤዲ ሱሌማን ጥምረት የፋሲል ተከላካይ ክፍልን በሚገባ መፈተን ችሏል።የሁለተኛው እጋማሽ የመጀመርያ ሙከራ ከቀኝ መስመር ኤዲ ሱሌማን ያሻገረው ኳስ አብሬይ ቼርሞ በግምባሩ ቢገጨውም ከግቡ ጎን ለጥቂት ወጥቷል።


በተመሳሳይ ቦታዎች ጥፋቶች ሲሰሩ የነበሩት ፋሲሎች ሁለተኛው እጋማሽ ላይ በእካል ብቃት ተዳክመው ታይቷል።በመጀመርያው እጋማሽ የኳስ ብልጫ ወስደው የተጫወቱት ፋሲሎች ሁለተኛ እጋማሽ ላይ ኳሱን ለእዛሞች በመስጠት መከላከልን ምርጫቸውን እድርገዋል።በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ በእዞሞች ጥቃት ደርሶባቸዋል፤በተለይ ተቀይሮ የገባው ሙዩ ኩሪ በተቀራራቢ ደቂቃዎች ከተመሳሳይ ቦታ የመታቸው ሁለት ኳሶች እንደኛው ለትንሽ ወደ ውጭ ሲወጣ ሁለተኛው የግቡ እግዳሚ ሊመልሰው ችሏል።መሃል ሜዳ ላይ ብልጫላይ የተወሰደበት ውበቱ እባተ ሁለተኛው እጋማሽ ተዷክሞ የታየውን ሃብታሙ ተኸስተን በሰለሞን ሃብቴ በመቀየር በተሻለ ሁኔታ ተከላካይ ክፍሉ ሽፋን እንዲያገኝ እድርጎ ጨዋታው በፋሲል እሸናፊነት እንዲጠናቀቅ እድርጓል።

በዚህም መሰረት ፋሲል ከነማ የመጀመርያው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታውን በማሸነፍ ጀምሯል።የመልሱ ጨዋታ ከ15 ቀናት በኃላ ታንዛንያ ላይ ይካሄዳል።


Report Page