አንዳንድ ግዜ...

አንዳንድ ግዜ...

አዥቬል
...ምድርን ዳግም ልፈጥራት ያምረኛል...

ከፍ ማለት እፈልጋለሁ። እንደ ንስር ከፍ ብሎ መብረር ያሰኘኛል። ነፋሱን እየቀዘፍኩ ምድርን ከፍ ብዬ ላያት እሻለሁ። ስደክም ሃይሌን እያደስኩ ከፍ ከፍ ማለት:ከፍታው ላይ ሆኜ ክፋትን ማየት:እንደ ብርሃን ፍጥነት ከላይ ወደ ታች ወደ ጥልቁ ተምዘግዝጌ ክፋትን ከምድር መንጭቄ ማውጣት። ምድርን እንዳሻቸው እየዋኙ ከሚያውኳት ፍጥረቶች ነፃ ማውጣት:ዝም ማሰኘት ያምረኛል።

ደግ የሆኑትን ደግሞ ከፍታ ላይ ሆኜ ከሚነጥቅ አሞራ ልታደጋቸው:ልጠብቃቸው እሻለሁ። ሞት እንኳን ሲመጣ ልናጠቃቸው ያምረኛል። ደጋግ ፍጥረታት የምድር ጌጥ ናቸውና ሁሌም ምድር ላይ እንዲኖሩ እሻለሁ። ተፈጥሮን ''ተው ባክህን!'' ብዬ መለማመጥ ያሰኘኛል....ቅኖች ሲሞቱ ያመኛል። ክንፌ የተቆረጠብኝ ያህል መሄጃ ይጠፋኛል....።

''እግዜር ምድርን ረገማት:እሾህ እና አሜኬላ አበቀለች'' እያሉ ቢነግሩኝም... ምርጡ ዘር እንዳይበቅል አንቀው የያዙ: የበቀሉትም እንዳያድጉ በክፋት ቃል የሚገድሉትን.. ምድር ላይ እንደ አሸን የበቀሉትን እሾህ እና አሜኬላዎቹን ከከፍታዬ ወደ ታች ተምዘግዝጌ ነቅልቅል አድርጌ ዳግም ላይበቅሉ ልጥላቸው ይሻለሁ....።


ምድርን ዳግም ልፈጥራት: ልባርካት ያምረኛል።
''ሰላም ሁኚ:የክፋት ዘር አይበቅልብሽም። እሾህና አሜኬላ ሊበቅሉብሽ አይቻላቸውም:እኔ ባርኬሻለሁና።'' ልላት እፈልጋለሁ.......ቢሆንልኝ....



Report Page