*/

*/

From

በዙምባቤው ምድር እንዲህ ሆነ…የሀገሪትዋ መሪ ጋብሬል ሮበርት ሙጋቤ ሀገራዊ ምርጫ ቢደርስም እስከመጨረሻዋ ቀን ድረስ ምንም ቅስቀሳ አላደረጉም ነበር። ለተቀናቃኛቸው ስልጣኑን አሳልፈው ሊሰጡ መስሎዋቸው የዙምባቤ ህዝብ በግምቱ ተደሰተ። ፧ በምርጫው ዋዜማ እለት ግን "ሙጋቤ ንግግር ሊያደርጉ ነው…ሁላችሁም በስታዲየም ተገኝታችሁ ንግግራቸውን መስማት ትችላላቹ"ተባለና ህዝቡ ስታዲየሙን አጥለቀለቀው። ስልጣን የሚያስረክቡ መስሎዋቸው በሀሳባቸው ለማን ይሰጡ ይሆን??እያሉ ስታዲየሙን ከአፍ እስከ ገደፉ ሞሉት። ከአፍታ ቆይታ በሁዋላ ሙጋቤ ከስታዲየሙ ደረሱ።መርፌ ቢወድቅ ይሰማል።ንግግራቸውን ለመስማት ስታዲየሙ ፀጥ ረጭ አለ። "የዙምባቤ ህዝብ ሆይ…!!እኔን ልትሰማ እዚህ ድረስ በመምጣትህ አመሰግናለው"ብለው ንግግራቸውን ጀመሩ። "ቅድሚያ በመጀመሪያ ስትመርጠኝ <ለራሴ ሰራው ከበርኩ> ። ለሁለተኛ ግዜ ስትመርጠኝ<ለቤተሰቦቼና ለዘመድ አዝማዶቼ ሁሉ ሰራው> ከበሩ። እንግዲ እኔም ከብሬያለው ፤ቤተሰብ ዘመድ አዝማዶቼንም እንዲከብሩ አድርጌያለው። ፧

ነገ በሚደረገው ምርጫ ለ ሶስተኛ ግዜ ከመረጥከኝ ግን ለህዝብ ነው የምሰራው።ለናንተ ነው የምሰራው።ይህ ግልፅ ነው……ነገር ግን ሌላን ሰው ብትመርጡ ግን መጀመሪያ ለራሱ ይሰራል።ይከብራል።ከዚያም ለሁለተኛ ግዜ እድል ከሰጠኸው ለዘመድ አዝማዶቹ ይሰራል።ለህዝቡ የሚሰራው ለሶስተኛ ግዜ ከመረጥከው ነው…

……ታዲያ በዚህ ወቅት እናንተን ለማገልገል የሚቀርበው ማን ነው???……እኔ ነኝ።

ስሜም ለሶስተኛ ግዜ የምመረጠው ጋብሬል ሮበርት ሙጋቤ እባላለው……ጨርሻለው።ነገ በምርጫ ወቅት እንገናኝ"ብለው ንግግራቸውን አበቁ።

የዙምባቤ ህዝብ ለሊቱን በጭንቀት ያለ እንቅልፍ አሳለፈ።በነጋታውም ራሳቸው ተመረጡ። ምርጫ ማጭበርበር ኮሮጆ መገልበጥ ብቻ አይደለም…አሳምኖ ድምፅን መዝረፍም ነው ምንጭ ፦ "ደህንነቱ ...ገፅ 135-136"

ደራሲ ፦ ይስማዕከ ወርቁ

Report Page