*/

*/

From

ዝግመተ ለውጥ (Evolution) ---

ሁለመናው (universe) በታላቁ ፍንዳታ (big bang) ከጀመረ ጀምሮ፣ እየሰፋ (expanding) ለመሆኑ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። ፍንዳታውን ተከትሎ የተለያዩ ኤለመንቶች (elements) በመቀላቀል (fusion) ወይም መለያየት (fission) ተፈጥረዋል። የእነዚህ ኤለመንቶች መሮርና የሙቀቱ ሁኔታ መመቸት ደግሞ ለህይወት ወሳኝ የሆኑ ኒኩሊክ አሲድ (nucleic acid = DNA + RNA) የሚሰራባቸው ኒውክሎታይድስ (neucleotides)፣ ፕሮቲን የሚሰራባቸው አሚኖ አሲድስ፣ የካርቦሃድሬት የሚሰራባቸው ሹገርስ (monosaccharides)፣ የቅባትና ዘይት (lipids) የሚሰራባቸው ፋቲ አሲድና ግላይሲሮል (fatty acid and glycerol) እንዲሆኑና እነዚህ ትላልቅና ለሕይወት አስፈላጊ ሞሊኪሎች እንዲፈጠሩ አግዟል። እነዚህ ትልልቅ ሞሊኩሎች በአንድ ላይ በብዛት በውሃ ውስጥ ሲገኙ ደግሞ ውሃን በመጥላት ወይም በመውደድ በሚያደርጉት መስተጋብር፣ ሁለት ደረጃ ያለው ነገሮችን መርጦ ማሳለፍ የሚችል የልፒድና የፕሮቲን ሜምብሬን ከውስጥ ኒውክሊክ አሲዶችን እንደ ጀነቲክስ ቁስ፣ ካርቦሃድሬትን ደግሞ ከውጭ በመያዝ መራባት፣ ሙቴት ማድረግ የሚችልና ዘገምተኛ ለውጥ ማካሄድ የሚችሉ ህያዋንን አስከተለ። በእርግጥ የመጀመሪያዎቹ ህያውያን ፕሮካርዮቶች (prokaryotes) ሲሆኑ በመቀጠል ደግሞ የተሻሉና በሴል ውስጥ የተለያየ ስራ የሚሰራባቸው ክፍሎች ያሏቸው ዩካርሮቶች (eukaryotes) መጠዋል። የዩካሮቶች አመጣጥ የአንድ ፕሮካሮት በሌላው የመዋጥ (symbiotic relationship) ይመስላል። የዩካሬቶች በአንድ መሰባሰብ ወይም የተባዙ ህዋሳት በበቂ ሁኔታ ክፍፍሉን አለመጨረስ፣ ቀስ በቀስ ግን እያንዳንዱ ኒውክለስ የራሱ ሜምብሬን እንዲኖአረው መሆን ባለ ብዙ ህዋስ ህያውያን እንዲመጡ አድርጓል።

ዳርዊን የተፈጥሮ ምርጫን አስተሳሰብ ከ3 የሚታዩ ነገሮች አንጥሮ ነበር ያወጣው፦ 1) እንስሳትም ሆነ እጽዋት ወደፊት ሊኖር ከሚችሉ ዘሮች በላይ አተረፍርፈው ነው እሚራቡት (ፈከንዲቲ); 2) ሕይወት ያላቸው እያንዳንዳቸው ነገሮች ሁልጊዜ የተለያየ ጸባይ ነው ያላቸው፣ ስለሆነም እያንዳንዳንቸው በቀጣይ የመኖር ዕድላቸው የተለያየ ነው (አዳፕቴሽን);

3) ስለሆነም የአንድ ማህበረሰብ አባላት ሲሞቱ፣ የሚገላቸውን ነገር ጠንክረው እሚቋቋሙት ግለሰቦች ብቻ በሕይወት ቆይተው ወደፊት መራባች ይችላሉ። ስለሆነም ቀስ በቀስ እነዚህ በህይወት ያሉ፣ በህይወት የሌሉትን አይነቶች እየተኩ ይሄዳሉ (ሴሌክሽን)።

በ20ኛው ክፍለ ዘመን ዳርዊን ያልደረሰበት ጄኔቲክስ (ሥነ በራሂ) እና ዝግመተ ለውጥ ተዋህደው ማህበረሰባዊ ጄኔትክስ እሚባለውን ጥናት ለመፍጠር ችለዋል። ይህም ሕይወት ያላቸው እያንዳንዳቸው ነገሮች ሁልጊዜ የተለያየ ጸባይ ነው ያላቸው፣ ስለሆነም እያንዳንዳንቸው በቀጣይ የመኖር ዕድላቸው የተለያየ ነው የሚለውን የዳርዊን ያሳብ ምክንያት ‘ጀነቲክ ሙቴሽን’ መሆኑን እንድናውቅ አግዞናል።

የዘገምተኛ ለውጥ ለህያዋን ወደዚች አለም መምጣት መንስኤ መሆኑ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የመረጃው መጠን እየጨመረ ከህልዮት ወደ እውነትነት ደርሷል። አሁንም ግን የዘገምተኛ ለውጥ በተነሳ ቁጥር በአማኞች የሚነሳው ጥያቄ፣ ዘገምተኛ የሆነ ለውጥ (gradual evolution) ከነበረ የሽግግር ቅሪቶች (transient/intermediate fossils) የት አሉ የሚል ነው። የዳሪውንና የዋላስ የዘገምተኛ ለውጥ (evolution by natural selection) ከአካባቢ ጋር በሚደረግ መስተጋብር የሚወሰን ነው። ይህም መንገድ የሽግግር ቅሪት ያለመኖሩን ምክንያት ለማስረዳት አልቻለም ነበር። በኋላ ግን የጀነቲክስ እውቀት በመጨመሩ ምክንያት ለውጥ የሚያመጡ ሙቴሽንስ (nonsynonymous mutations)፣ የፕሮቲንን ቅርጽን ብሎም ስራውን በመወሰን ከአካባቢ ጋር መስተጋብር በመፍጠር የእያንዳንዱን ህያው ህልውና ይወስናሉ፣ መኖር ወይም አለመኖርን። ነገር ግን በፕሮቲን ላይ ምንም ለውጥ የማያመጡ ሙቴሽንስ (missense/synonymous mutations) ወይም ለውጥም ቢኖር ተመሳሳይ ቅርጽና ፀባይ ያላቸው አሚኖ አሲዶች የሚተኩበትም ሁኔታ አለ። ይህም በፕሮቲኑ ስራ ተጽእኖውን በመቀነስ ብዙ ሙቴሽንስ በረጅም ጊዜ እንዲጠራቀሙ፣ ከዚህ ያለለውጥ ረጅም ጊዜ በኋላ ግን ፈጣን ለውጥን እንዲመጣ ያደርጋል። ይህም ሂደት ነው፣ የሽግግር ቅሪቶች እንዳይኖሩ ያደረገው። ለዚህም በቂ የሆነ መረጃ በMolecular theory of Evolution ጥናት የተገኘ ሲሆን ይህም ሂደት Panctuated Equilibrium ይባላል።

Report Page