🅗🅐🅟🅟🅨 🅑🅘🅡🅣🅗 🅓🅐🅨

🅗🅐🅟🅟🅨 🅑🅘🅡🅣🅗 🅓🅐🅨

꧁༒ًٍٰٰٰٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̰̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃saintJo༒Ꮻ꧂

...ምግባር ነኝ እንደ ድንገትም ቢሆን ይህን ደብዳቤ እየሰማሽ ከሆነ ይህን ልንገርሽ ከልቤ ፈለኩ እና ብዕሬን ፈልጌ ይህንን ፃፍኩልሽ...በርግጥ በአካል ፊት ለፊትሽ ሆኜ ብነግርሽ ምን ያህል ደስ ይለኝ ነበር የእውነቴን ነው...


 እንዴት ግን አንድ አንድ ታሪኮች ሳይጀምሩ ያልቃሉ ወይንም ደሞ ገና በደንብ እንኳን ሳይጀምሩ በቃ ይባላሉ...ደስታን ያወቅነው ሀዘን ስላለ ነው...አብሮ መሆንን አብዝተን የተመኘነውን አብሮ አለመሆንን ወይንም ብቸኝነትን ስለምናውቅ ነው...


 አሁን ላይ ብንገናኝ፣ብናወራ እና አይን ለአይን ባንተያይም አውቃለሁ አንቺም ታውቂያለሽ የአንቺን ደስታ ብቻ እንደምመኝ... በሄድሽበት ሁሉ መልካሙን እንደምመኝልሽ እና ሰለ ሰላምሽ ሁሌ እንደምፀልይ...ታውቂያለሽ...


 የሚሰማው ሰው ካገኘ ሁሉም ለፍላፊ ነው...ብዙዎች የሚያወሩት እና ዝምታን የመረጡት የሚያወሩት አጥተው ሳይሆን የሚያወሩለት አጥተው ነው...


 ሁሉም ፊቱን ቢያዞርብሽ...ቀን ቢጎልብሽ...የምትወጂያቸውን ብታጪ...በብርሀን ቢጨልምብሽ እኔ አለሁ...የእውነቴን ነው...በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ ካስፈለኩሽ ና በይኝ...እመኚኝ እመጣለሁ...ብዙ ሰው ሊወድሽ ይችላል...በጣም ብዙ ሰው...ነገር ግን ጌታን እንደእኔ የሚወድሽ አይኖርም...


እኔ እወድሻለው… ምን ያህል ግን እኔጃ…አላውቅም…ግን የእውነት እወድሻለው …አሁን እማመሰግንበት ምክንያት ብዙ ነው… ከሁሉም በላይ ግን አንቺ በህይወቴ ስላለሽ ነው…

yene konjo


በቃላት መጠበብ ባልችልም... ልክ እንዳንቺ ድምፄ ቀልብን ባይገዛም ልክ እንደራሴ ራሴን ሆኜ ምኞቴን ፃፍኩልሽ...


😔በዚቸ ራስ ወዳድነት በገነነባት... እኔነት ሚዛን በደፈባት አለም እንኳንም ተወለድሽ አልልሽም!


😒በዚች ሰላም ልክ እንደሰማይ በራቀባት...ጦርነት ስንት ህፃናትን በሚቀጥፍበት 

እናት እያየች ልጇን በምታጣበት በዚች ሰቆቆናም አለም እያየሁ እንኳንም ተወለድሽ አልልም!


😑ሴት ወጣቶች ሳያድጉ በሚቀጩበት...ሳይፈኩ በሚጠወልጉበት አለም እንኳንም ተወለድሽ ብዬ አልመኝልሽም!


🥺ሚበላ ባልጠፋ ስንቶች በሚራቡበት አለም እንኳንም ተወለድሽ አልልም!


😥ከሚያምረው ውብ ቦታ... ከኤደን ገነት ወደዚች ቀፋፊ አለም ስለመጣሽ እንኳንም ተወለድሽ ልልሽ አልችልም!


🙂ግን መወለድሽ መቼ ብስራት እንደሚሆንብኝ ታውቂያለሽ... ፍቅሬ

ልክ ስልኬን አንስቼ ያንቺንን ድምፅ ስሰማው ስለኬን ከፍቼ ፎቶሽን ሳየው ያኔ መወለድሽ ብስራት ይሆንብኛል🥰 ...


🥳መወለድሽ ያስደስተኛል ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?


እኔነት የበዛበት አለም ብዬ በፈረጅኳት አለም... እንዳንቺ አይነት ፍቅርን የሚሰጥ፣ ይቅርታን የሚሰብክ ሰው ስላለ እንኮን ተወለድሽ እላለው።


ይቺ ጦርነታም ባልኳት አለም ድምፅሽን ስሰማ የመልዕክትሽ ና የድምፅሽ ማማር ልቡን ያጀገነ ክፉ ጦረኛንም ሆድ እንደሚያርድ... ልቡን እንሚያሸፍትበት...ሳስብ ያኔ እንኳንም ተወለድሽ እላለሁ!


🙃መወለድ ሁሉም ይወለዳል... በህይወት መኖራችንን ምናውቀው ግን የተፈጠርንበትን ምክንያት ስናውቅ ነውና... በህይወት ስላለሽ ደስ ብሎኛል..

አሁን እንኳንም ተወለድሽ ብያለሁ!!!

19-11-2012 ይቺ ቀን እናትሽ ከነብሷ ነብስ 

ከስጋዋ ስጋ 

ከደሟ ደም 

ከመልኳ ሳትሰሰት ራሷን የሰጠችሽ ቀን ስለሆነ እናትሽንም እንኳንም ተወለድሽ በይልኝ መወለዷን ባንቺ አይታለችና!!!!!!!


ብዙ ነገር ካንቺ እጠብቃለሁ!!!


ንግስቲቱ ተወልደሻል 

ንግስቲቱ ተወልደሽ አድገሻል 

እርቃኑን ወደዙህች ምድር የመጣ ሁሉ ባነቺ መኖር ባለጸጋ ሆኗል፡፡ጸጋው #ሳቁ ነው፡፡ ጸጋው አንቺ ባለሽበት ቦታ ሁሉ ሀሴትን መሸመት ነው።


ልቤ ሁሌ ይጠብቅሻል

 #ደስታ #ሀሴቴ 

 #ክብሬ #ኩራቴ

#መታወቂያዬ #መለያዬ

ስትስቂማ አይጣል ነው 


አንዳንዴ የኔ መኖር ምንድነው ጥቅሙ ለምንስ እኖራለሁ ብዬ ራሴን ስጠይቅ ልቤም አእምሮዬም በአንድነት እንዲሁ ይሉኛል "አንተ እኮ ለሷ ነው የምትኖረው።ሙሉ መኖርህ የሷ ነው ይለኛል ደስ በሚሉ ቀናት… ደስታ በሞላቸው እና እሚያልፉ በማይመስሉ ውብ ቀናትም መሐል አንቺ ልቤ ውስጥ ነበርሽ … መንገዱ አድክሞኝ መንገድ ዳር በወደኩበትም ቀናት ቢሆን አንቺን አረሳሁሽም።


 እናም ምን ለማለት ነው የመኖሬ ምክንያት የሆነሽው ምርጥዬዋ እና ተወዳጇ ፍቅሬ ዛሬ ነው ልደትሽ እናም

#ንግስቲቱ ተወልደሻል

#ንግስቲቱ ተወልደሽ አድገሻል

#ንግስቲቱ ዛሬ ነው ልደትሽ 


እስከ ዛሬ ባሳለፍናቸው ቀናትቶች ውስጥ ምንም ቅር የሚለኝ ነገር የለም…ባደረግናቸውም ይሁን ባላደረግናቸው ነገሮች በሙሉ ደስተኛ ነኝ…ደሞ ደስታሽ ደስታዬ ነው ስኬትሽ ስኬቴ…💝💖💝💖


 አስታውሳለው ካንቺ ጋራ ሆኜ ከማንም ጋር አልነበርኩም ስለማንንም አላስብም ነበር አሁንም ብቻዬን ወጣለው የተቀየረ ነገር የለም የተቀየረው ነገር ቢኖር ያንቺ አለመኖር ብቻ ነው።


የሆነ ልደብቅሽ የፈለኩት ነገር ነበር ግን አልቻልኩም ናፍቀሽኛል ከምታስቢው በላይ ናፍቀሽኛል አብረን ያሳለፍናቸው ቀናቶች እጅግ ናፍቀውኛል።


ቻው አልልሽም ምክንያቱም ድጋሜ ላይሽ ፈልጋለው ተመስገን ነወ ይህን ያህልም ከኖርን በቂ ነው።


ሀፒ ሀፒ በርዝ ደይ ሀፒ በርዝ ደይ  


መልካም ልደት ይሁንልሽ እንኳንም ተወለድሽልኝ የኔ ፍቅር 


HAPPY BIRTH DAY


መልካም የልደት ቀን!!!

 


ያንቺው አፍቃሪ king mg

Report Page