.......

.......

Li Ta


... ዕለት ዕለት እላዬ ላይ የሚደረብ የትዝታ በርኖስ አለ። የኖርኳት ኩርማን ጊዜና ያልኖርኩባቸው ዘመናት ትዝታ ነፍሴን ተጭነዋታል። ከኖርኩት በላይ የማላውቀው በትዝታ ይወዘውዘኛል። ከሚያጔጔኝ ምናፍቀው ይበልጣል። ህልምሽ ሲሉኝ አልጋዬ ላይ እየተገላበጥኩ ስለማስበው ካቻምናና ሳልፀነስ በፊት ስለነበረው ጊዜ ልነግራቸው እዳዳለሁ። ልቤ እንደ መቃብር ባለ የሀዘን ፀጥታ ተሞልቷል ። የነፍሴን ስር አየሰረሰረ ድካም ሲወረኝ ይሰማኛል። ጊዜውን እንደጨረሰ ሽማግሌ ነፍሴ ልትጎብጥ ዘልሳለች። የእድሜዬ ጠዋት ላይ ቆሜ ስለመድከሜ መናገር አፍራለሁ። ያልኖርኳቸው ቀናቶቼ በመታዘብ የሚገረምሙኝ ይመስለኛል። 'ምኑን ኖርሽውና' መባል ያስፈራኛል። ይሄን እያልኩ አንገቴን ጠምዝዤ የሚያነክስ እግሬን እየጎተትኩ እንደዘመኑ ወግ እንደ እኩዬቼ ልሆን እባክናለሁ...


Report Page