♦♦♦♦

♦♦♦♦

N🅰🅿🅾

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 3 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታኒያ ኢትጵያን ጨምሮ በታዳጊ ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የ 15 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ ይፋ አደረገች፡፡

[Natnael yared](https://t.me/zNatnael)

ድጋፍን በዛሬው ዕለት በጀመረው የሁለት ቀናት የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ የብሪታኒያ የአፍሪካ ጉዳች ሚኒስትር ሀርየት ባልድዊን ይፋ አድርገዋል፡፡


ይፋ ከሆነው የ15 ሚሊየን ፓውንድ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ፕሮግራም መካከል 12 ሚሊየን ፓውንዱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በታዳጊ ሀገራት የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነትን ለማረጋገጥ የሚውል ነው፡፡


የአፍሪካ ጉዳች ሚኒስትር ሀርየት ባልድዊን 3 ሚሊየን ፓውንዱ ደግሞ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የመናገር እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን ለማረጋገጥ እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡


በዛሬው ዕለት ይፋ ሆነው ይህ ፕሮግራም ብሪታኒያ በተያዘው ፈረንጆች ዓመት በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ያደረገችውን ድጋፍ ወደ 27 ሚሊየን ፓውንድ ከፍ አድርጎታል፡፡


ይህ ድጋፍ በሀገሪቱ የአለም አቀፍ ልማት መምሪያ በኩል ተደራሽ እንደሚሆን ነው የተነገረው፡፡

Report Page