*/

*/

Source
BBC News Amharic
በኤርትራ ምርጫ ተካሂዶ የማያውቀው ለምንድን ነው?
------------------------------------------------- የኤርትራ ሕዝብ፤ በ1983 ዓ.ም ነጻነቱን ካገኘ በኋላ በዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት የሚመራ መንግሥት ለመትከል ለ30 ዓመታት ቢጥርም፤ እስከ ዛሬ ሕገ መንግሥቱ ሥራ ላይ ሳይውል፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሳይካሄድ ቆይቷል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ይህ እንደሚሆን የሚታይ ፍንጭ የለም። የአገሪቷ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ያልፈቀዱበት ምክንያት ምንድን ነው? የኤርትራ የነጻነት ትግል ሻዕቢያና የኤርትራ ነጻነት ትግል [ተሓኤ] "ቅኝ ግዛትን በማስወገድ ሕገ መንግሥታዊና ዴሞክራሲያዊ ነጻ ኤርትራ" መገንባት የሚል አላማ ይዘው መታገላቸውን ኤርትራን በቅርበት የሚከታተሉ ምሁራን ይናገራሉ። በሳሕል በተካሄደው ሁለተኛው ጉባኤ [እኤአ 1987] የወጣው አገራዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራም እንዲሁም በ1994 (እኤአ) በተካሄደው ሦስተኛው ጉባኤ የጸደቀው አገራዊ ቻርተር አላማው "ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ መንግሥት መፍጠር" እንደነበረ የሕግ ሙሁር ዳዊት ፍስሃየ ይናገራሉ። "ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መመስረት" በሚል ርዕስ በ1987 የተዘጋጀው ፕሮግራም "የትግሉ አላማ የሕዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ መንግሥት መመስረት ሆኖ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነጻ የሕዝብ ወኪል፣ ሕገ መንግሥት የሚያረቅ፣ አዲስ ውሎች የሚያጸድቅ፣ የዜጎች መብቶች የሚያስከብርና ሕዝብን የሚያገለግል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቆም" እንደነበረ ያስረዳል። በ1994 የጸደቀው ቻርተር ደግሞ፣ አገራዊ የዴሞክራሲ ፕሮግራም ሃሳብን የሚያነሳ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ መጎስ ብርሃነ በበኩላቸው፤ "ሕግና ሥርዓት የሚያከብር፣ አንድነትና ሰላም የሚያስጠብቅ፣ አገራዊ አንድነት የሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት" ያለመ ነበር ይላሉ። በ1990 ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የድርጅታቸው ሊቀመንበር በነበሩበት ወቅት፤ ሁሉም እንደየአቅሙ አገር በመገንባትና በአገሪቷ ላይ በሚገነባው ሥርዓት ተሳታፊነት እንዲኖረው፣ ሁሉንም የሚወክል ሥርዓት እንዲመጣ፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርሥት እንዲገነባ፤ አንድ ፓርቲ የሚመራው የፖለቲካ ሥርዓት ግን መረጋጋትና ዋስትና እንደማይፈጥር መግለጻቸውን ያስታውሳሉ።

ሙሉውን ለማንበብ፦https://bbc.in/3fDEbmL

Today at 1:01 AM · Public · in Timeline PhotosView Full Size

የኤርትራ ህዝብ ለ30 አመታት በጦርነት የተማገደው በከንቱ ነው፡፡

2 · Today at 1:46 AM

የናንተ አይነት "ዘጋቢ" ስላልተገኘ ነው።ከድሮ ደ
ዘመዶቻችሁ 100% ምርጫ/ቅርጫ 100% ይሻላል።loser.

Edited · 2 · Today at 1:47 AM

በ 6ኛው ሀገረዊ ምርጫ በ ኢትዮጵያ እናት ፓርቲ ለሀገር እና ለሕዝብ ምቺ መደላድል መርሀግብር ቀርጻለች።

ምን አገባህ አንተ ቦቅቧቃ ሌባ።

Today at 2:40 AM

What difference could it make. We had fake BBC elections where one party won all the time they didn’t have any elections and one guy ruled all g to be time. Same same.

10 hours ago

እንደ ህወሀት የውሸት ምርጫ ከማድረግ ብለው ይመስለኛል!ማስመሰል አይችሉበትም!

5 hours ago

Peresdant Esayas is authcratc leder.

5 hours ago

ቢቢሲ ለምንድ ነው የኤርትራ ጥሩ የማይዘግበው?

Play Video

1 · 8 hours ago

ከኢሳያስ አፈወርቂ ውጪ ማንም እንዲመራን ስለማንፈልግ ነው።

32 minutes ago

ምርጫ ቦርድ ስለሌላቸው ይመስለኛል

Today at 4:17 AM

 View more comments…

Report Page