💔💔💓💞💞

💔💔💓💞💞

Abinet

ይሄን ስጽፍልሽ እንዴት ባለ በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆኜ እንደሆነ በዚህ በውድቅት ሌሊት እኔ እና ፈጣሪ ብቻ ነን የምናውቀው፡፡ አንቺን ባሰብኩ ቁጥር አሁንም የማላውቀው ፍርሃት ይወረኛል፡፡ እራሴን ‹‹ለምን›› ብዬ እጠይቀዋለሁ፡፡ ግን መልሱን አላቀውም፡፡ 


ጊዜው በጣም ይሮጣል፡፡ አንድ ቀን ነበር ድንገት ነጠላ ያደረገች፣ ቀይ እና የደስ ደስ ያላት፣ ፈገግታዋ የሚገርም ያቺን ቆንጅዬ ልጅ ያየሁዋት፡፡ ይኸው አሁን እንደምንም አንድ አመት ሞላ፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር ልደታ ድራማ ለመስራት Direct ሳደርግ ያገኘኋት፡፡ በወቅቱ ለጥበብ እና ለስራ የነበራት ፍቅር የሚደነቅ ነው፡፡ ላስተካክላት ስሞክር ‹‹ሃሳብ አይግባህ በሰዓቱ አሳምንሃሉ›› ስትለኝ የምታሳየኝ ፈገግታ እና በራስ መተማመን በጣም ይገርመኝ ነበር፡፡ ግን እንዲህ ከምንም በላይ የማፈቅራት እና የምወዳት ልጅ ትሆናለች ብዬ በፍጹም ጠብቄ አላቅም፡፡ ስራው ካለቀ ቦሃላ ግን እራሴን አሁንም ድራማው ቦታ ቀርቶ አገኘሁት፡፡


በእሷ ምክንያት የእውነት ማፍቀርን አየሁት፣ እውነት ለካ መውደድ እንዲህ ነው አስባለችኝ፡፡ በአንድ በኩል በአገልግሎት በኩል የማቃትን ልጅ ለፍቅር በመመኘቴ ከህሊናዬ ጋር አሟገተችኝ፡፡ ‹‹ባንተ ምክንያት ከአገልግሎት ብትቀርስ›› ብሎ ህሊናዬ ሲጠይቅ ውስጤ ይንቀጠቀጣል፡፡ ‹‹አንተ መሰናከያዋ ብትሆንስ›› ብሎ በጥያቄ ያጣድፈኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እርሷን ያፈቀረው ውስጤ በሕይወትህ ውስጥ ካላመጣሃት ብሎ በናፍቆት ያስጨንቀኛል፡፡ እንዲህ ያለ ፈተና በሒወቴ ገጥሞኝ አያቅም፡፡ ቆሜ ሳስተምር እንኳን እርሷ ከተቀመጠችበት ማየት ይከብደኛል፡፡ ለደቂቃ ተሳስቼ ያየሁ እነደሆነ ሃሳቤ ተሰውሮኝ እደናበራለሁ፡፡ ባፈቀረው ውስጤ እና በስጋቴ መሃል ለዓመት ያህል ብዙ ተቸገርኩኝ፡፡ 


ካንተ በላይ እግዚአብሔር ይቅደም ብሎ ውስጤ አሳመነኝ እና በቃ እንደ ድሮው አንደ እህቴ ለማየት ትግሌን ጀመርኩ፡፡ በቃ ለአገልግሎት የከፈልከው ዋጋ ይሁን ብሎ ውስጤ አሳመነኝ፡፡ ነገር ግን ፍቅሯ - ዘልዬው መሄድ የከበደኝ ትልቅ ቋጥኝ ሆነብኝ፡፡ ልረሳት ሞከርኩ፣ ሞከርኩ፣ ግን . . . . ፡፡ ትግሌ መና ሆነብኝ፡፡ ትዝታዋን ከውስጤ ነቅሎ ማውጣት ከበደኝ፡፡ ሞከርኩ በጣም ለቀናት አይደለም ለወራት ሞከርኩ፡፡ አቃተኝ እርሷን ትቶ ማለፍ፡፡ እርሷን ረስቶ ማለፍ ከበደኝ፡፡ የእውነት በሕይወቴ እንዲህ ያለ ስሜት ተሰምቶኝ አያቅም፡፡ በውስጤ እምቅ አድርጌ ለ1 ዓመት አፈቀርኳት፡፡ በተለይ የዘንድሮን ዓመት በፍቅሯ ሕይወቴ ምስቅልቅል አለ፡፡ ፈተና ደርሶ እንኳን ትምህርቴ ላይ ማተኮር እስኪያቅተኝ ድረስ እርሷን ማሰብ መተው አቃተኝ፡፡ የእውነት እንዲህ ያለውን ጥልቅ ፍቅር በሕይወቴ አስቀመሰችኝ፡፡

ፍቅሬ ልክ እንደ ፀሐይ ናት፡፡ ከሩቅ ስታያት በፈገግታዋ ደምቃ ትማርካለች፡፡ ማስተዋል እና ጥበብን የተሞላች ናት፡፡ በራስ መተማመኗ ከእሷ አልፎ ቢታደል ላገር የሚበቃ ነው፡፡ ስትቀርባት ደግሞ የምታቃጥል ፀሐይ ናት፡፡ የሚማርከው ፈገግታዋ ሲነሳ የሚያስፈራ፣ የእርሷ የማይመስል ቁጣዋ አለ፡፡ ስትቀርባት ታቃጥላለች፡፡ ግን ይኼን ቁጣዋን እኳን ለመጥላት መውደድ አቅም አሳጥቶኛል፡፡ እርሷ ማለት በሩቅ እንደምትታይ እንደ ጽጌ ረዳ ናት፡፡ ከሩቅ ፈገግታዋ - እንደ መዓዛው ይስባል፣ ደም ግባቷ - አይንን ይማርከል፡፡ ሲቀርባት ግን ደግሞ ሌላኛው እሷነቷ እንደ እሾሁ ይዘነጣጥላል፡፡ ቁንጅናዋ፣ ስብዕናዋ ከሩቅ ይስበኛል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ብዙ ነገሮች ልቀርባት ስል እንደ እሾሁ በፍርሃት ይዘነጣጥሉኛል፡፡ 


ግን እስቲ ዛሬ እንኳን ከውስጤ ይውጣ ትንሽ አረፍ ልበል፡፡ በጣም እወዳታለሁ፣ በጣም አፈቅራታለሁ›› እርሷን ትቼ ሕይወቴን መቀጠል አቅቶኛል፡፡ ሁለ ነገሯ በውስጤ ውስጥ ግዘፍ ነስቷል፡፡ በጣም ስለምወዳት በጣም እፈራታለሁ ግን ደግሞ በቃላት ከምገልጸው በላይ አፈቅራታለሁ!!! . . . . አዎ በጣም አፈቅራታለሁ፡፡ she is the pain in my head and the blessing in my life. አሁን በቃ ይብቃኝ እውነታውን መጋፈጥ፡፡ ልረሳት አልችልም፡፡ ሌላ ሁለተኛ ዓመት ይህን ስቃይ ለመጋፈጥ አቅም የለኝም፡፡ ልወድቅ ትንሽ የቀረኝ የተንጋደደ ዛፍ ነኝ፡፡ ወይ ቀና ታርገኝ ወይ ገፍታ ትጣለኝ፡፡ ወይ በበረከትነቷ ቀና እላለሁ ወይ እወድቅና አፈሩን አራግፌ አንድ ቀን እነሳለሁ፡፡  አንድ ቀን . . . .!!!

እባክህን ውስጤ ለምን ለሶስተኛ ሰው ታወራለህ ለምን ለራሷ አትነግራትም ብለህ አታስጨንቀኝ፡፡ እውነታውን ታቅ የለ!!

(29-08-2012)  11፡00 PM

Report Page