*/

*/

Source

የግድያ ዛቻ እየተሰነዘረበት ያለው ግብፃዊው ሀቀኛ ኢንጂነር
ሱሌማን አብደላ
ኢትዮጵያን ያለ ስሟ ስም መስጠት ጥላቻ እንጅ መርህ አይደለም። በዘመነ ታሪኳ የአባይን ውሀ ከልክላን አታውቅም።

«.ግብፃዊዩ ኢንጂነር »

ኢትዮጽያዊያን የአባይን ውሃ ወደ እኛ እንዳይመጣ ሊከለክሉት አይችሉም። እነሱም ፍላጎት የላቸውም።

ሊከለክሉ ቢፈልጉ ከሺ አመታት በፊት ባሰቆሙት ነበር ፥ ለእርሻ ፈልገው ቢገድቡት ኖሮ ገና ዱሮ ባደረጉት ነበር ፥

የአባይ ውሃ ከፈጣሪያችን የመጣ የሁላችንም ስጦታ ነው። የአባይ ግድብ በግብፅ ላይ አንዲትም የሚያሳርፈው ተፅዕኖ የለም።

ይሄንን በማለተቱ፦ ጋዜጠኛው በቁጣ እንዴት ይሄንን ትላለህ ብሎ ጠየቀው ?

የኢንጅነሩ መልስ፦ ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ በኛ በግብፃዊያን ላይ ምንም አይነት የውሀ እጥረት አያጋጥመንም።

ጋጤጠኛው በብስጭት እንዴት ይሄንን ትላለህ ? ሚሊየን ግብፃውያን እያዪህና እየሰሙህኮ ነው አለው

የኢንጅነሩ መልስ፦ ምናልባት አዎ ይሄንን ስናገር የሚበሳጩ ግብፃውያን አይኖሩም አልልም። እኔ ለምናገረው ነገር ሙሉ
በሙሉ ሀላፊነቴን እወስዳለሁ።

ሙያየ ኢንጅነር እንጅ ፖለቲካ አይደለም። ሙያየ ኢንጅነር እንደመሆኑ መጠን ሙያየን የማከብር እስከሆንኩ ድረስ ለሀቅ እናገራለሁ።

ምክኒያቱም ኢትዮጵያዊያን ሚሊዮን ዶላር አውጥተው የሚሰሩት ግድብ የኤለክትሪክ ሀይል ለማመንጨት ነው። በራሳቸው ገንዘብ በሰሩት ግድብ ሀገራቸውን ከድህነት ለማውጣት ነው እንጂ እኛን ለመጉዳት ብለው አይደለም። ኢትዮጵያውያን እንዲህ አይነት ፀባይ የላቸውም። ታሪካቸው ይህን አያሳይም።

የናይል ውሀ በክረምት እጅግ ይጨምራል
እነሱ ሀገር ማሻአላህ ዝናብ አለ።

በዝናብ ውሀ አከማችተው ኤሌክትሪክ “ካመነጩ” ቡሀላ ውሀውን ወደኛ ይለቁልናል።

ከለቀቁት ቡሀላ ውሀው ወደኛ እንጂ ወደየትም አይሄድም። ስለዚህ ግድብ ስለተገነባ የግብፅ ድርሻ አይቀንስም።

ኢንጀነሩ ይሄንን በማለቱ ከጋዜጠኛው በግብፆች ከፍተኛ ስድብን እያስተናገደ ነው .

የተወያዩትበት፣ የቪዲዮ ክርክር ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በዚህ ሊንክ ይገኛል

https://m.youtube.com/watch?v=Omn7MpZ8H1E&feature=youtu.be .

ሱሌማን አብደላ

Report Page