*/

*/

Source

ግርማይ አዲስን ያያችሁ!!
በህይዎት መኖሩን ወይም አለመኖሩንም የምታውቁ እባካችሁ መረጃ ስጧቸው!! መልኩን የማያውቁት ሴት ልጆቹ አባታቸውን ናፍቀዋል!! የልጆቹ እናት የዘመናት ናፍቆቷና ፍቅሯን ፍለጋ እየተንከራተተች ነው!!

ግርማይ አዲስ ተወልዶ ያደገው ደሴ ከተማ ከቀድሞው የህጻናት ሆስፒታል ወረድ ብሎ ወደ ዳወይ ሜዳ በሚያሻግረው የቦርከና ወንዝ ዳርቻ ላይ ነው፡፡ ግርማ የደሴ ሆጤ ሜዳ ካፈራቸው ምርጥ እግር ኳሰኞች መካከል የሚጠራ ለወሎ ክ/ሃገር ፖሊስ (ዋሊያ) እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ውድድር አ/አበባ ላይ ሲካሄድ ባሳየው ምርጥ ብቃት በአሰልጣኝ ንጉሴ ገብሬ ምርጫ ለኦሜድላ ክለብ ተመርጦ በወቅቱ አ/አበባ እንዲቀር ተደርጓል፡፡

ግርማ አዲስ አበባ በቆየባቸው ጊዜያት ከተዋወቃት ፍቅረኛው (የልጆቹ እናት) ወ/ሮ ብዙአየሁ 2 ሴት ልጆችን ያገኘ ቢሆንም ባልታሰበ አጋጣሚ የት እንዳለ/እንደሄደ ሳይታወቅ ጠፍቶባቸዋል፡፡ ልጆቹ ዛሬ ላይ ግን ትልቅ ልጆች ሆነው የማያውቁት አባታቸው ያለበት አለመታወቅ ረፍት ነስቷቸው ናፍቆታቸውን እያቀጣጠለ የህይዎታቸው ትልቅ እንቆቅልሽ ሆኖ በተሰበረ ልብ ነገን በተስፋ በተሞላ ስሜት እየናፈቁ ዛሬን በአባታቸው ፍለጋ ተጠምደው እያሳለፉት ነው! ትልቋ ልጁ ቤተልሄም ግርማ ትባላለች “አባቴ ለሰርጌ ቀን ይመጣል::” እያለች በጉጉት እየጠበቀችው ነው፡፡ ታናሷ ትዝታ ግርማ የክረምት ዝናብ ያሳቅቃታል ምናልባት አባቴ በረንዳ ላይ ወድቆ ችግር ላይ ይሆናል ብላ ትሰጋለች፡፡ የልጆቹ እናት ባለቤቱ ከዓመት በዓል ድባብ ጋር ተቆራርጣለች ባሏን እያስታወሳት ከፍቷት ስለምትውል!!

ይህን አሳዛኝ ታሪክ ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=etF75YW1v5Y
የእምዬ ደሴ ልጆች በተለይ የቀድሞ የወሎ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር አባላት ምናልባት መረጃ ካላችሁ እባካችሁ አድርሷቸው፡፡

Report Page