*/

*/

Source

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፐሮገራም በድጋፍ ያገኘውን የሚዲያ መሳሪያዎች ለማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች አስረከበ
************************************************
15/08/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን (ኢመብባ) ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በድጋፍ ያገኘውን የሚዲያ መሳሪያዎች ለማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች አስረከበ፡፡

የሬዲዮ መሳሪያዎቹ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አማካኝነት ከ76 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ወጪ ተደርጎ የተገዛ ሲሆን አስር የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ያለባቸው የአቅም ክፍተት በጥናትና በመስክ ምልከታ ተለይቶ ድጋፉ ተደርጓል፡፡

በርክክብ ፐሮገራሙ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ምክትል ተወካይ አቶ ክሊዮፓስ ቶሮሪ ተግኝተዋል፡፡

በርክክብ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬከተር የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች በአከባቢው ህዝብ ባለቤትነት የተያዙና ከይዘት ዘገባ አንፃርም ከንግድ ፍላጎት ነፃ በሆነ ሁኔታ በበማህበረሰቡ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ በመሆናቸው ለሰላምና ለአብሮነት የሚያበረክቱት አስተዋፆ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም አቅማቸው እንዲጎለብት፤ እንዲስፋፉና ተደራሽነታቸው እንዲጨምር ባለስልጣኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንና ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ምክትል ተወካይ አቶ ክሊዮፓስ ቶሮሪም በበኩላቸው የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች መደበኛዎቹ መገናኛ ብዙኃን ተደራሽ ባልሆኑበት አከባቢ ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ በመሆን ለዜጎች ማህበራዊ እድገት የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፐሮግራም ለዘርፉ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ጥራታቸውን የጠበቁ ካሜራዎች፣ ሚክሰሮች፣ ኮሚፒውተሮች፣ የድምፅ መቅረጫዎች እና ኤል ሲ ዲ ሞኒተሮችን የመሳሰሉ እቃዎች በድጋፉ ውስጥ ይገኙበታል፡፡

Report Page