*/

*/

Source
Technology and Innovation Institute, Ethiopia
የሶፍትዌር ማሻሻያ እየጠበቀች ማርስ ላይ ያለችው የናሳ ሔሊኮፍተር
****************************************** ከጥቂት ቀናት በፊት በማርስ ውስጥ የተለያዩ ቅኝቶችን ለማድረግ ታስባ የተሰራችው ሄሊኮፍተር ከምድራችን ውጭ የቅኝት በረራን የምታደርግ የመጀመሪያዋ ሄሌኮፍተር ተብላ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ማርስ ላይ ያለበረራ ተቀምጣለች፡፡ የህዋ ምርምር ኤጀንሲው ሄሊኮፍተሯ የሶፍተዌር ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋት ተናግሯል፡፡ የምርምር ተቋሙ ይህን ይበል እንጂ የሄሊኮፍተሯን የአካል ክፍል የሚከታተሉ ኢንጅነሮች በውጨኛው ተሸከርካሪ ክፍል (rotor) ላይ ችግር እንዳስተዋሉ ተናግረዋል፡፡ ኢንጂነሮቹ ባስተዋሉት ችግር ምንያት ኢግኒዩቲ የተሰኘችው አነስተኛ ሄሊኮፍተር የሙከራ በረራዋ እንዲዘገይ አድርገዋል፡፡ ችግሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ መፍትሔዎችን በማፈላለግ ላይ ያሉት ኢንጅነሮቹ የሙከራ በረራውን ለማድረግ ጥረቶችን እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እንደ ናሳ መረጃ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት የተሻለው ሀሳብ የሄሊኮፍተሯን ሶፍትዌር ማሻሻል ነው፡፡ በናሳ ውስጥ የጄት ምርምር ቤተሙከራ የኢግኒውቲን ተልእኮ እየመራ ሲሆን የተሸሻለውን ሶፍትዌር በመሞከር ላይ ሲሆን ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ወደ ማርስ ለመላክ እንደታሰበ ተነግሯል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ጥቂት ጊዜ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ አሁን ላይ ሄሊኮፍተሯ ከሀይል፣ ከግንኙነትና ከሙቀት አንጻር በታሰበው ልክ ያለች ሲሆን ሄሊኮፍተሯን ተሸክሞ ወደ መልክዓ ማርስ የወሰዳት ሮቭረም ያለምንም ችግር እየሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እንደተመራማሪዎቹ ሀሳብ ከሆነ የኢግኒዩቲ በረራ ዋና ተልዕኮው የምርምር ስራ ሳይሆን የቴክኖሎጂ ሙከራ ነው፡፡

ምንጭ ፡ Independent

5 hours ago · Public · in Timeline PhotosView Full Size

Wushatamoch Nasa Canada Beach Lay Quc Bilew Mars Yilalu Meret Zirg Nat We Are Under The Dome

4 hours ago

amazing brain blowing

2 hours ago

ሲጀመር ማርስ ላይ ያለው የአየሩ ግፊት ና ይዘት (Atmospheric pressure &volume )በጣም አነስተኛ ስለሆነ ድሮኗ ለመብረር ትቸገራለች።

5 hours ago

Report Page