*/

*/

Source

የኢትዮጵያ ልጆች የስፔስ ክህሎት ማሳደጊያ ማዕከል በይፋ ተመሰረተ
---------------------------------------
ሚያዝያ 04/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ልጆች የስፔስ ክህሎት ማሳደጊያ ማዕከል በይፋ ተመሰረተ፡፡

በአለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1961 ወደ ህዋ በመጓዝ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ራሺያዊ ጠፈርተኛ ዩሪ ጋጋሪ 60ኛ አመት የስፔስ ጉዞ መታሰቢያ በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ተከብሯል።

በመርሀግብሩ ላይ የራሺያ ፌዴሬሽን ተወካይ ሚካኤል ኮርኔቭ የተገኙ ሲሆን፣ ተተኪ የስፔስ ሳይንስ ልሂቃን ልጆችን ለማፍራት የሚያስችል የኢትዮጵያ ልጆች የስፔስ ክህሎት ማሳደጊያ ማዕከልም በይፋ ተመስርቷል።

የዘንድሮው 60ኛ አመት የስፔስ ጉዞ የመታሰቢያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ እና በኢትዮጵያ የራሽያ ኤምባሲ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠፈርተኛው ዮሪ ጋጋሪ ወደ ህዋ ያደረገውን 60ኛ አመት ጉዞ ከመዘከር በዘለለ የአዲሱ ትውልድ ተረካቢ የሆኑ ወጣቶች ስለ ህዋ የበለጠ እንዲሳቡና እንዲነሳሱ ተስፋ የሚሰንቁበት ዝግጅት ነው ተብሏል።

የስፔስ ሳይንስ ዘርፉ ከ120 አመታት በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና ራሽያ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ተናግረዋል።

የራሺያ ፌዴሬሽን ተወካይ ሚካኤል ኮርኔቭ በበኩላቸው፣ የራሽያዊው ዮሪ ጋጋሪ ወደ ጠፈር በመሄድ ቀዳሚ በመሆን ለበርካቶች ምሳሌ፤ ለአለም ታሪክ ደግሞ ቀዳሚ መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያም በዚህ ዘርፍ ላይ እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች የስፔስ ክህሎት ማሳደጊያ ማዕከል ይህንን ግንኙነት ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ በስፔስ ሳይንስ ዘርፉ እውቅና በተሰጣቸው እና በዘርፉ ልዩ ዝንባሌ እና ተሰጥኦ ባላቸው ታዳጊ ልጆች ስራ ይጀምራል ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ የስፔስ ጉዞ አውደ ርዕይ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ልጆች የስፔስ ልህቀት ማዕከል የመጡ ተማሪዎች ትምህርታዊ ገለፃ ተደርጓል።
(በቁምነገር አህመድ)

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/WALTATVEth

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን

https://twitter.com/walta_info


አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!

Report Page