*/

*/

Source

የቢትኮይን ማይኒንግ በየአመቱ 37 ሚሊዮን ቶን የካርቦን ልቀት እያስከተለ ነው
===========================
ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ዋጋው አሽቆልቁሎ የነበረው ቢትኮይን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ወጋው እየጨመረ መጥቶ አሁን ላይ ከ56 ሺ ዶላር በላይ ደርሷል፡፡ ይህ ዲጂታል መገበያያ የተፈላጊነቱ መጠን እጅግ በያለ ቁጥር ወደአለማችን ይዞት የሚመጣው የአካባቢ ብክለተም በዛው ልክ እየጨመረ እንደሚመጣ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በቅርቡ ይፋ ተደርጎ በነበረ ጥናት በቢትኮይን ማይኒንግ ሂደት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ኔዘርላንድ እና አርጀንቲና በየአመቱ ጥቅም ላይ ከሚያውሉት በእጅጉ በልጦ እንደሚገኝ ያሳየ ነው፡፡ አሁን ከሰሞኑ የወጣ ጥናት እንደጠቆመው ከሆነ ደግሞ በቢትኮይን ማይኒንግ የተነሳ 37 ሜጋ ቶን ወይም 37 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የካርቦን ፉትፕሪንት በየአመቱ ወደከባቢ አየር እንደሚለቀቅ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ምጣኔም እንደ ኒውዝላንድ ያሉ ሀገራት በየአመቱ ወደ ወደከባቢ አየር ከሚለቁት የካርቦን መጠን ጋር የሚስተካከል ነው፡፡

በቻይና መቀመጫውን ያደረገ አንድ የምርምር ተቋም በሀገሪቱ በቢትኮይን ማይኒንግ የተነሳ በቀጣይ አመታት ሊኖር የሚችለውን የካርቦን ልቀት በማጥናት እስከ 2024 ድረስ የሚኖረውን ምጣኔ የተነበየ ሲሆን፤ በዚህም በቀጣዮቹ አመታት ከ130 ሚሊዮን ቶን በላይ የካርቦን ፉትፕሪንት በቢትኮይን ማይኒንግ የተነሳ ብቻ ወደ ከባቢ አየር እንደሚለቀቅ አስቀምጧል፡፡ 75 በመቶ የቢትኮይን ማይኒንግ የሚካሄድባት ቻይና በዚህ የካርቦን ልቀት አደጋ ውስጥ ዋና ተጠቃሽ ሀገር ስትሆን የሌሎች ሀገራት ምጣኔ ተደምሮ ሲታይም የቢትኮይን ማይኒንግ ዘርፍ ካበድ ችግር ወደአለማችን እየጠራ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፡፡

የቢትኮይን ማይኒንግ የዲጂታል ገንዘብ ልውውጥ ስርዓቱ በትክክል መፈፁምን ለማረጋገጥ በሚሰሩ miners ተብለው በሚጠሩ ከፍተኛ የኮምፒውተር አቅም ባላቸው ሰዎች የሚካሄድ የኦንላይን ውድድር ሲሆን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያስፈልጋቸው ሰርቨሮች የሚካሄደው ይህ ፉክክርም የኦንላይን ግብይቶቹን አረጋገግጦ ክፍያ ለማግኘት በሚደረግ ውስብስብ የሂሳብ እንቆቅልሽን የመፍታት እንቅስቀሴ ነው፡፡ ይሄ አሰራር “distributed computation” የሚባል ሲሆን ዋና ዓላማውና ጥቅሙም የመረጃ ልውውጡና አስተዳደሩ በአንድ ተቋም ስር ሳይወድቅ ለሳይበር ጥቃት የማይመች ማድረግ እና የመረጃ ትክክለኝነቱ “data integrity” ዋስትና እንዲጠበቅ ማድረግ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቢትኮይን ዋጋ እንዲህ ለመጨመሩ ዋና ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው እንደ ቴስላ፣ ማስተርካርድ እና ቢ ኤን ዋይ ሜሎን ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ታዋቂውን ክሪፕቶከረንሲ በከፍተኛ ሁኔታ በመግዛታቸው እና ሌሎች ትልልቅ ድርጅቶችም የክፍያ ስርዓታቸውን ወደዚህ የቢትኮይን አሰራር እየቀየሩ በመምጣታቸው እንደሆነ ይነገራል፡፡ ለአብነት ኤለን መስክ የሚመራው ቴስላ በአክስዮን ገበያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ካላቸው ኩባንያዎች በቀዳሚነተ የሚቀመጥ ሲሆን ይህ ኩባንያ በቅርቡ 1.5 በሊዮን ቢትኮይን ከመግዛቱም ባለፈ አንዳንድ ምርቶቹን በዚህ የክሪፕቶከረንሲ ለመገበያየት ማቀዱ የቢትኮይንን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረው እና የአካባቢ ብክለት ስጋቱም በዛው ልክ እንዲያል ምክንያት እንደሆነ ይገለጻል፡፡
ምንጭ፡ cnbc እና nature

Report Page