*/

*/

Source

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በንጉሠ ነገሥት ዙፋን ከተቀመጡ በኋላ (1922 ዓ.ም.)በግንቦትና በሐምሌ ወር አዋጆች እንዲነገሩ አደረጉ። ከአዋጆቹ አንዱ የሐሰት ወሬ ያወራ ሰው እንዲቀጣ የታዘዘበት ነው። ቃሉም ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው። አዋጅ በየጊዜው ነገር እየፈጠርህ ያልሆነ ወሬ ታወራለህ፣ አሁንም በሐሰት ወሬ የተነሣ እርስ በእርሣችን ደም ከመፋሰስ አገር ከመበደል ደረሰ። ከእንግዲህ ወዲያ ግን አየሁ ብሎ የማይመሰክርበትን ሐሰት ነገር አውርቶ የተገኘ፣ ፈጥሮ ያወራው የመንግሥትን ነገር የሚነካ የሆነ እንደሆነ እንደ ጥፋቱ መጠን ቅጣት ይፈረድበታል። በሌላውም ነገር ሰው ሐሰት ያወራው ባለ ቀሚስ* የሆነ እንደሆነ አራት መቶ ብር ያልተሾመ ሰው ሲሆን ሁለት መቶ ብር መቀጫ እየከፈለ እኩሌታው ለከሳሹ ተሰጥቶ እኩሌታው ወደ መንግሥት ይግባ። ይህንንም መቀጫ መክፈል የሚያቅተው ሰው እንደ ገንዘቡ ግምት ታስሮ ሥራ በመሥራት ይክፈል። (ምንጭ፦ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት) *ባለ ቀሚስ= ባለ ሥልጣን

ነገር ፈጥሮ ማውራት ያልለመደበትን Terara Network ተራራኔትዎርክ ላይክ ሼር እና ሰብስክራይብ ያድርጉ ለማለት ነው። 😉

Report Page