*/

*/

Source

እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን !
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ወደ ኮምፕሬንሲቨ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታልነት ያደገበትን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ተረክቧል

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ክቡር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሐብታሙ አበበ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ልዩ ምስጋና አቀረቡ

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ክቡር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሐብታሙ አበበ እንደተናገሩት የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል በዩኒቨርሲቲዉ ስር እንዲተዳደር ከተደረገ ጀምሮ የሆስፒታሉን ታካሚዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እና እርካታን ለማሳደግ በተለይም የእናቶችን እና የጨቅላ ህፃናትን ሞትን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን፤

በዋናነትም በህክምና ሙያ የሰለጠኑ ብቁ ባለሙያዎችን ከሞላ ጎደል እንዲሟሉ ጥረት መደረጉ ፤ የሆስፒታሉን የአገልገሎት አሰጣጥ ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ ልዩ ልዩ አዳዲስ የህንፃ ግንባታዎችን በማካሄድ የህክምና አገልግሎቶችን መስጫ ልዩ ልዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ደረጃቸዉን እንዲጠብቁ በማድረግ እንዲሁም ልዩ ልዩ ለህክምና እጅግ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ሟሟላት መቻሉን አስታዉሰዋል::

ፕሬዝደንቱ አያይዘዉም የሆስፒታሉ እድገት መገለጫ ሊሆን የሚችለዉን ወደ ኮምፕሬንሲቨ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታልነት ያደገበትን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሆስፒታሉ ማገኘት በመቻሉ ፤ የሆስፒታላችንን የማኔጀመንት አባላትን እና ሁሉንም የሰራ ሃላፊዎች፥ ሁሉንም ሀኪሞች የጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞችን በእጅጉ የሚያስመሰግናቸዉ እና የሆስፒታሉን ክቡራን ተገልጋዮች የሆኑት የሀድያ ዞንና አጎራባች ዞኖች ታካሚዎችንና ሁሉንም የአከባቢ ማህበረሰብ ክፍል ደግሞ የሚያስደስት መሆኑንም ገልፀዋል::

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሐብታሙ አበበ አክለዉ እንደገለፁት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ሆስፒታሉ ያቀረበዉን ጥያቄ ተከትሎ ወሳኝ የሆነ ኢንስፔክሽን እንዲደረግ በመፍቀድ ብቻ ሳይወሰን፤
በዋ/ዩ/ን/እ/መ/መ/ሆስፒታል ልዩ የሆነ የኢንስፔክሽን ቡድን ልኮ የቡድኑ አባላትም በሆስፒታሉ በአካል ተገኝተዉ ጥሩ የሆነ ኢንስፔክሽን አድርገዉ ከተመለሱ በሁዋላ በአጭር ግዜ ውስጥ በቀልጣፋ የአሰራር ሂደት ፈጣን ምላሽ በመሰጠቱ ለጤና ሚኒስቴር ልዩ ምስጋና አቅርበዋል ፕሬዝደንቱ::የእንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን ! የሚል መልዕክታቸዉንም ለመላዉ የአከባቢዉ ህብረተሰብ፣ ለሆስፒታሉ የማኔጀመንት አባላትና ለሁሉም የሰራ ሃላፊዎች፥ ለሁሉም ሀኪሞች ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች
አስተላልፈዋል::

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዳነ ደስታ በበኩላቸዉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ሆስፒታሉን ወደ ኮምፕሬንሲቨ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታልነት እንዲያድግ የሚያስችለዉን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠበት ዋነኛ ምክንያት በባለፉት ጥቂት ዓመታት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስር ሆስፒታሉ ከመተዳደሩ ጋር ተያይዞ በተገኘዉ መጠነ ሰፊ ዕድል በሆስፒታሉ የሰለጠኑ የህክምና ባለሙያዎችን ፣እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ማሟላት በመቻሉ እና የልዩ ልዩ Especiality and sub Especiality በመከፈቱና በአጠቃላይ ሆስፒታሉ ተፈላጊዉን ሙያዊ፣ ድርጅታዊ እና ሌሎች መስፈርቶችን በሟሟላት በተደረገዉ ኢንስፔክሽን ተረጋግጦ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር አዋጅ 661/2002 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2ሠ መሰረት በማድረግ እንደተሰጠ አስታዉቀዉ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል::

ዶ/ር አዳነ ደስታ አክለዉም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ወደ ኮምፕሬንሲቨ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታልነት ያደገበትን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት መቻሉ ወደ ፊት ሆስፒታሉ መጠነ ሰፊ እድገት ለማምጣት ያለዉን ሰፊ እድል ስለሚያረጋግጥ ፤ ይህንኑ እድገት ተከትሎም ሆስፒታሉ ለህብረተሰቡ የሚሰጠዉን ዘርፈ በዙ ጠቀሜታ ስለሚያሰፋ ፤
ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ትልቅ ደስታ ነዉ በማለት እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን ! የሚል መልዕክታቸዉንም ለመላዉ የአከባቢዉ ህብረተሰብና ለሆስፒታሉ የማኔጀመንት አባላትና ለሁሉም የሰራ ሃላፊዎች፥ለሁሉም ሀኪሞች ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች አስተላልፈዋል::

27/07/13 ዓ.ም ዘገባዉ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነዉ::

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

Report Page