*/

*/

Source

የመጀመሪያው የማርስ ላይ ከተማ እቅድ
******************************
የስነ-ህንጻ ተመራማሪዎች ለቀዩዋ ፕላኔት የመጀመሪያ የሆነ 250,000 ሰዎችን ማኖር የሚያችል በዋሻ መልክ የሚገነባ የከተማ ዕቅድ ይፋ አደረጉ፡፡ ይህ ከተማ ኑዋ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን ስያሜውንም ያገኘው በቻይና ከሚነገሩ ተረቶች በአንዱ አምስት ድንጋዮችን በማቅለጥ ጠንካራ ምሰሶ ያለው ቤት ከሰራው ጣኦት ስም እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከዚህ ሀሳብ ጀርባ እንዳለው እንደ ABIBOO መረጃ ከሆነ አንድ ሰው ወደማርስ ለጉብኝት ለመሔድ በሚከፍለው ሶስት መቶ ሺህ ዶላር ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ የተሟሉለትን ከተማም የመጎብኘት እድል አለው፡፡ በከተማው የሚገነቡት ቤቶች ከ25 አስከ 35 ስኩየር ሜትር ስፋት የሚኖራቸው ሲሆን በዚያ የሚኖሩ ሰዎችም ከ60 እስከ ሰማንያ በመቶ የሚሆነውን የስራ ሰዓታቸውን የሚያሳልፉት በከተማዋ በሚሰጥ ስራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በማርስ ለመኖር በዋናነት ራስን ከአደገኛ ጨረር ለመጠበቅ የሚያስችል መከላከያ የሚያፈልግ መሆኑን ያስታወሰው የስነ-ህንጻ ምርምር ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም ሁሉንም ምግብ ከምድር መውሰድ ስለማይቻል ማርስ ላይ የምግብ ሰብሎችን ለማምረት የሚያስችል ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበትም እምነቱን ገልጧል፡፡ እነዚህን ሁለት መሰረታዊ ችግሮች ለመቅረፍም ተቋሙ ሶኔት ኔትወርክ ከተባለ የምሁራን ስብስብ ጋር አብሮ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ የተመራማሪዎች ስብስቡ ቴምፔ ሜንሳ የተባለ የማርስ አካባቢን ለይተዋል ሲል የመረጃ ምጫችን ዘግቧል፡፡

ABIBOO አክሎም ሰዎች በተለየው አለታማ አካባቢ በተሰሩ ዘመናዊ ዋሻዎች የሚኖሩ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ሌሎች ለጨረር የተጋለጡ አካባቢዎችን አስፈላጊ ሲሆን ብቻ እንደሚጎበኙ ገልጧል፡፡ ለትራንስፖርትም ከጥብቅ አካባቢው ውጭ መንቀሳቀስ የሚችሉ ባቡሮችና አውቶቢሶች የታሰቡ ሲሆን በጥብቅ አካባቢው ወይም ለመኖሪያ በተሰራው አካባቢ ደግቦ ትላልቅ አሳንሰሮችን ጥቅም ላይ ለማዋል ታቅዷል፡፡

በመኖሪያ ክልሉ መሰረት አካባቢ መልኣ ማርስን መመልከት የሚያስችሉ የተለያዩ ማማዎች እንደሚሰሩ እና ከአደገኛ ጨረር ለመጠለል የሚያስችሉ ተንቀሳቃሽ ጣሪያዎችም ይገነቡላቸዋል ተብሏል፡፡ የመኖሪያ መንደሩ አስፈላጊ የሚባሉ እንደ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት፣ የገበያ ስፍራዎች፣ የስፖር ማዘውተሪያዎችና ዩኒቨርሲቲዎችም የተሟሉለት ነው፡፡

የማርስ ላይ ከተማ እቅዱ ከምግብ ሰብሎች በተጨማሪም የተለያዩ እንስሳትንም ያካተተ ነው፡፡ ምንም እንኳን ኤሎን ማስክ በ2050 የማርስ ላይ ከተማው እውን እንደሚሆን የተናገረ ቢሆንም የABIBOO ቃል አቀባይ ግን እስካሁን የከተማ ግንባታው የሚጀመርበት ጊዜ እንዳልታወቀ እና በ2054 ይጀመራል የሚል ሀሰተኛ ወሬ እንዳለም ተናግረዋል፡፡
ምንጭ Popular Mechanics

Report Page