*/

*/

Source

ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አስራ ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 13
አንዲት ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም ወይስ ትሸከማለች?

A. አትሸከምም፦
35:18 *“ኀጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላዋን ሸክም አትሸከምም”*፤ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌۭ وِزْرَ أُخْرَىٰ

B. ትሸከማለች፦
16፥25 ይህንንም የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ *”ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው”*፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ! لِيَحْمِلُوٓا۟ أَوْزَارَهُمْ كَامِلَةًۭ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ ۙ وَمِنْ أَوْزَارِ ٱلَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ

መልስ ከላይ ያለውን አጠያየቅ ከአንሰሪንግ ኢሥላም ላይ በትክክል ስላላስቀመጡት እኔ በትክክል አስቀምጬላቸዋለው።

በቁርአን እስተምህሮት ውስጥ እንደ ክርስትናው “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ማለትም እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት የለም፤ ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም፤ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾቹ ላይ፦ “ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም” እያለ ይነግረናል፦


17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

እዚህ ድረስ ከተግባባን የሚቀጥለውን አንቀፅ እንዲህ መረዳት ይቻላል፦
16፥25 ይህንንም የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ *”ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው”*፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ! لِيَحْمِلُوا أَوْزَارَهُمْ كَامِلَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۙ وَمِنْ أَوْزَارِ الَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ أَلَا سَاءَ مَا يَزِرُونَ

አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲያሳስት አሳሳቹ በማሳሳቱ ምክንያት የተሳሳተው ሰው የሚያገኘውን ቅጣት ከሚሳሳተው ላይ ቅጣቱ ሳይቀነስ ሳይጨመር የተሳሳተውን ሰው ቅጣት አሳሳቹ ይቀበላል፤ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ከመራ መሪው በመምራቱ ምክንያት የተመራው ሰው የሚያገኘውን አጅር ከሚመራው ላይ አጅሩ ሳይቀነስ ሳይጨመር የተመራውን ሰው አጅር መሪው ይቀበላል፤ ከላይ ያለው መልክእት ይህ ነው፤ ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀፅ በሐዲስ እንዲህ ይፈስረዋል፦ ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210

አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ጥመት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚሸከሙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ይሸከማል፤ ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ምሪት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚያገኙትን ምንዳ ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ያገኛል"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ أَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى ضَلاَلَةٍ فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أَوْزَارِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أَوْزَارِهِمْ شَيْئًا وَأَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى هُدًى فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أُجُورِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا ‏”

ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም ማለት ለምሳሌ መቶ ኪሎ ጤፍ ተሸክሜ ከነበረ ሌላ ሰው ለእኔ ጤፉን ከተሸከመልኝ እኔ ላይ መቶ ኪሎ ጤፍ የለም ማለት ነው፤ ግን አጥማሚ የጠመመውን ሰው በእርሱ ምክንያት ነውና ከእርሱ ቅጣት ሳይጓደል ይቀጣል፤ ለምሳሌ ቃየል የአደም ልጆች መግደልን ያስተማረ ነው፤ ሰዎች ሰው በገደሉ ቁጥር ገዳዩ ሊቀጣበት ያለውን ቅጣት ቃየልም ይቀጣል፤ ያ ማለት ገዳዩ ቅጣቱ ይቀልለታል ማለት አይደለም፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 28, ሐዲስ 38

ዐብደላህ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“በግፍ ገዳይ አንድም ሰው የለም፥ የእርሱ ወንጀል ድርሻ በመጀመሪያው የአደም ልጅ ላይ ቢሆን እንጂ፤ ምክንያቱም እርሱ ግድያን በማስተዋወቅ የመጀመሪያ ነበር"*። عَنْ عَبْدِ، اللَّهِ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لاَ تُقْتَلُ نَفْسٌ ظُلْمًا إِلاَّ كَانَ عَلَى ابْنِ آدَمَ الأَوَّلِ كِفْلٌ مِنْ دَمِهَا لأَنَّهُ كَانَ أَوَّلَ مَنْ سَنَّ الْقَتْلَ ‏”

ስለዚህ አላህ በሰው ቀኝና ግራ ባሉት መላእክት የሚከትበው ሰዎች የሰሩትን መልካምና ክፉ ስራ ብቻ ሳይሆን “ፈለጎቻቸውንም” ማለትም ያጠመሙትን ወይም የመሩትን ስራ ጭምር ነው፤ አንድ ሰው በመመሳቱ ብቻ ሳይሆን በማሳሳቱም ይጠየቃል፦
36፥12 እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ *”ያስቀደሙትንም ሥራ እና ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን”*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا وَآثَارَهُمْ ۚ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ فِي إِمَامٍ مُّبِينٍ

ቀጥሎ ያለውን ውዥንብር ተመልከቱ፦ "አላህ በመሐመድ"ﷺ" ዘመን የነበሩትን አይሁድ አባቶቻቸው በሠሯቸው ኃጢኣቶች ሳብያ ሲወቅሳቸው እንመለከታለን፦
2፥51 ሙሳንም አርባን ሌሊት በቀጠርነው ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ ከዚያም ከእርሱ መኼድ በኋላ *”እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን አምላክ አድርጋችሁ ያዛችሁ”*፡፡ وَإِذْ وَٰعَدْنَا مُوسَىٰٓ أَرْبَعِينَ لَيْلَةًۭ ثُمَّ ٱتَّخَذْتُمُ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَنتُمْ ظَٰلِمُونَ

ይህ ከውርስ ኃጢኣት ጋር አንዳች ግንኙነት የውም። ይህ ጥቅላዊ አይሁዳውነትን የሚያሳይ እንጂ በተናጥል የአበውን ወንጀል ወደ ልጆች መሸከምን አያመለክትም። አላህ ደመናን ያጠለለውና መናን እና ድርጭትን ያወረደው በሙሳ ዘመን ቢሆንም በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ወደነበሩት አይሁድ፦ "በእናንተም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በእናተም ላይ መናን እና ድርጭትን አወረድን" እያለ ይናገራል፦
2፥57 *”በእናንተም ላይ”* ደመናን አጠለልን፡፡ *”በእናተም ላይ”* መናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ

"እናንተ" የሚለው ጥቅላዊ አነጋገር እንጂ በነቢያችን”ﷺ” ዘመን የነበሩት አይሁድ ደመናም አልጠለለላቸውም፥ እንዲሁ መናን እና ድርጭትን አልወረደላቸውም። አላህ ወደ ነብያት ያወረደው በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ወደነበሩት አይሁድ እና ክርስቲያን “ወደ እናንተ አወረድን” ማለቱንም አስተውሉ፦
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ *በሉም፦ «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን”*፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

ስለዚህ "እናንተ" የሚለው ሃይለ-ቃል ጥቅላዊ መልእክት እንጂ በተናጥል የአበውን ወንጀል ለልጆች መተላለፉን በፍጹም አያሳይም። አበው ጥጃ በማምለካቸው ልጆችን እየወቀሰ ነው ማለት ነው ብሎ መሞገት ለአበው ደመናን አጠለልን፥ መናን እና ድርጭትን አወረድን የሚለውን ለልጆች ምን አደረገ ብሎ መረዳት ይቻላል? ይህ የቂል እንጉልፏቶ አስተሳሰብ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

Report Page