*/

*/

Source

የኤፍራታ ግድም ወረዳ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ጥቃት እየደረሰብን ነው አሉ። ESAT

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ የአጣዬ፣ የማጀቴና የካራ ቆሪ ነዋሪዎች ትላንት ምሽት 4 ሰዓት ጀምሮ የኦነግ ሸኔ ቡድን ጥቃት እያደረሰ መሆኑን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለኢሳት ገልፀዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ኦነግ ሸኔ በኤፍራታ ግድም ወረዳ አጎራባች የኦሮሚያ ልየ ዞን ቀበሌዎችን ተገን በማድረግ በአጣዬ ከተማ፣ በካራ ቆሪ ከተማና በማጀቴ ከተማ ገብቶ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት እያደረሰ ይገኛል፡፡

ይህ ዘገባ እየተጠናቀረ ባለበት ሰዓት ለጣቢያችን የደወሉ ነዋሪዎች ቡድኑ የከፈተባቸውን ጦርነት ለመመከት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ አክለውም እስካሁን የተደራጀ የመንግስት የፀጥታ ሃይል ወደ ስፍራው አልደረሰም ብለዋል፡፡

የኦነግ ሸኔ ቡድን ግን በተደራጀ መልኩ ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ጥቃት እያደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን በነበረው የተኩስ ልውውጥ በአጣዬ ከተማ ሁለት፣ በማጀቴ ደግሞ ሁለት ንፁሃን ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡

መንግስት በአስቸኳይ ገብቶ አካባቢውን እንዲያረጋጋም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን የሰነዘረው በወረዳው ተመድበው የነበሩ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላት ለሌላ ተልዕኮ ወደ ክልል መወሰዳቸውን ተከትሎ እንደሆነም ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

(መጋቢት 11 ፣ 2013 ኢሳት አዲስ አበባ)

Report Page