*/

*/

Source

ጌታቸው ረዳ ዛሬ ካለበት ለ TMH ይኸን ብሏል።
#FastMereja

- ጦርነት አልቋል የሚባለው ምኞት እንደሆነ : ጦርነት ያልተካሄደበት ቀን እስካሁን እንደሌለ : ጦርነት አልቋል የሚባለው ተረት ነው::

- የነ አብይ ትልቅ የጦር መሳርያ ሆኖ ያለው : ትግራይ ከመላው አለም መገናኘት የምትችለውን ኮሙኒኬሽን በመዝጋት እነሱ የሚሉት ነገር ብቻ እውነታ ሆኖ የሚቀልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው::

- የትግራይን ህልውና ለማጥፋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለማክሸፍ የሚያስችሉ : ህዝባችን ወጣቱ ከዳር እስከ ዳር እየተነቃነቀ ነው:: መነቃነቁ መቀጠል መቻል አለበት::

- የኤርትራ ሰራዊት በተመለከተ ፈርኔሎ የሚዘርፍ አለ : ያረጀ ፎጣ የሚለብስ አለ : ሁሉም አይነት አላማ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ሀይል ነው::

- በአሁኑ ሰአት መሬታችን የማስለቀቅ ጉዳይ ተደርጎ ብቻ መወሰድ የለበትም :ህልውናችን ላይ የተቃጣ አደጋ ስለሆነ : ይህንን የህልውና አደጋ ለመፍታት በሚያስችል ደረጃ በስፋት መንቀሳቀስ ይኖርብናል ብለን : በዛ ላይ ተመስርተን እየተንቀሳቀስን ነው ያለነው::


ብርሃኑ ጁላ አስመልክተው ከተናገሩት

- ጦርነቱን በበላይነት የሚመሩት ያሉት የኤርትራ ጀነራሎች ናቸው:: ስለዚህ ብርሃኑ ጁላ ገፋ ቢል ስራ ቢኖረው የኤርትራ ጦር ቃል አቀባይ ሆኖ መናገር ብቻ ነው::

- እነ ብርሃኑ ጁላ : በላይ ስዩም ገፋ ቢል ፓዚሽን ቢኖራቸው የኤርትራ ቃል አቀባዮች ናቸው::

ኢትዮጵያ እና ትግራይ በተመለከተ

- ኢትዮጵያን መቀጠል አለባት ብለው በጣም በፅኑ ከሚያምኑት የህወሓት አመራሮች አንዱ ነኝ ብየ ነው የማምነው : በአሁኑ ሰአት ትግራይን ነጥሎ በተለይ በተለይ : ሌላው ይቅር እና ከጠላት መንግስት ጋር በመተባበር ትግራይን ለማዘረፍ : የትግራይ መሰረተ ልማቶችን ለማውደም : የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ : የትግራይ ህዝብ ለማዋረድ በስፋት የሚሰሩ የአማራ ኤሊት ግዛቴ በሚላቸውን መሬቶችን ለማስመለስ በሚል ሰበብ የጋራ ጠላት ስለተገኘ : በዚህ ላይ ተመስርተው የትግራይ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለው ግፍ ግምት ውስጥ አስገብተህ : እኔ አደባባይ ላይ ወጥቼ ኢትዮጵያ እናቴ የሚለው ቋንቋ የምችልበት ሰአት አይደለም አሁን::

- ኢትዮጵያ መቀጠል አለባት/የለባትም በሚለው ጉዳይ ላይ የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ውሳኔ መወሰን ያለበት መብቱም የሆነ የትግራይ ህዝብ ነው:: በአሁኑ ሰአት አጀንዳችን ከምንም ነገር በላይ ትግራይ ከወረራ ነፃ የምትወጣበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው:: ያ ካደረግን በኃላ የትግራይ ህዝብ የሚወስነውን ውሳኔ የምንቀበል ነው የሚሆነው::

- ትግራይን ለማንበርከክ (ጦር ሜዳ ላይ ብቻ አይደለም) : ጦር ሜዳ የተተኮሰብን እንችለዋለን : እየተሰዋንም እንችልዋለን ምንም ችግር የለውም:: ከጦር ሜዳ ውጪ ያሉ የትግራይ ተወላጆችን : በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን ለማንበርከክ : ለማቆኛረት እየተደረገ ያለው ስራ ይህንን ይዘህ ስለ ኢትዮጵያዊነት መስበክ እጅግ ከባድ የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብል ብቻ በቂ ነው::

ከአለም ጋር ያለው ግንኙነት በተመለከተ

- በምንፈልገው ደረጃ እየተገናኘን ነው ማለት አንችልም : መገናኘት በጣም ከባድ ነው:: ውሱን የኮሙኒኬሽን አቅም ግን ከደጋፊዎቻችን ጋር : በርካታ መንግስታት በርካታ የአለም ተቋማት ድጋፍ እንዳለን እናውቃለን : ምክንያቱም በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ወንጀል ተራ ወንጀል አይደለም:: ትልቅ ግፍ ነው እየተፈፀመ ያለው : ትልቅ አደጋ ነው እየተፈፀመ ያለው : ማንኛውም ህሊና አለኝ የሚል ወገን በሙሉ ሊያወግዘው የሚገባ ነው:: ግንኙነታችን አጥጋቢ ነው ማለት አንችልም:: ምክንያቱም የኮሙኒኬሽን ችግር አለ::

- ከሌሎች ጋር ያለን ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችለውን ስራዎች እየሰራን ነው:: ኢንተርናሽናል ኮሚኒቲ ጋር በሚቻለን ለመገናኘት እየሞከርን ነው::

- እንደዛም ሆኖ አለም አቀፍ ማ/ሰብ ከሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ በተሻለ ስለ ጉዳዩ ግንዛቤ ያለው እንደሚመስል ግን ማረጋገጥ ችያለው::

- ዋና ትኩረታችን አሁን የትግራይ ህዝብ ህልውና የሚወሰነው አሜሪካኖች በያዙት አቋም : ጀርመኖች በያዙት አቋም... አይደለም : የትግራይ ህዝብ ለህልውናው ሲል በሚከፍለው መስዋእትነት ነው:: በተግባርም እያረጋገጥነው ያለው ይሀው ነው:: ስለዚህ ይሄን በሚመለከት ወጣቱ ከየቦታው እየጎረፈ ነው::

ምርኮኞች በተመለከተ

- ጁንታ የሚባል እንዳለ በቅርቡ ነው የሰማሁት : ጁንታው የሚባል የሆነ ደካማ አውሬ የሚፈልጉ አይነት ተደርጎ ነው የሚላኩት: እነዚህ ጋር ፀብ የለንም:: ጦርነት ቢደረግ እንደ ቅጠል የሚረግፉት የሚያሳዝነው እነሱ ናቸው : መኮንኖቻቸውን መርጠን የምንገድልበት እድሉ ሲኖር መኮንኖቻቸውን እንገድላለን ችግር የለውም : የመግደል ችግር የለም እዚህ : ግን ተማርከው ሲመጡ : ምንም በማይውቁ ብዙ ህፃናት ላይ ለመጨከን የሚያስችል ልቦና ማንም ሊኖረው አይችልም::

የትግራይ ወታደራዊና ፓለቲካዊ ቁመና በተመለከተ

- ግምገማ በየጊዜው እንገመግማለን:: የአመራር ለውጥ ለማድረግ ምክንያት የለንም : አስፈላጊም ነው ብለን አናምንም:: ኮሌክቲቭሊ ነው የምንመራው አሁን::

- ስለዚህ በምናደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ይሁን የህዝቡ ሁኔታ የወገን ሁኔታ እያጠናን : አሁን ከተሞች የማስለቀቅ ጉዳይ ውስጥ የምንቻኮልበት ምክንያት የለም:: ከተሞቻችን የራሳችን ናቸው የትም አይሄዱም : ከተሞቻችን የጠላት አውድማ እንዳይሆኑ የሚቻለንን እናደርጋለን::

- መሬቶቻችን ማንም አጉሯ ዘለል ገብቼ ይዥያለው ስላለ : ይዝዋቸው እንደማይቀጥል እናውቃለን:: በቅርቡ በደንብ ማየት ትጀምራላችሁ:: በዚህ ደረጃ መሰራትን ያለበት ስራ እየሰራን ነው : እየሰራን እንቀጥላለን::

- ሰራዊታችን በየጊዜው ያሉበትን ድክመቶች እየገመገመ : ስልጠናዎች እያካሄደ ጠንካራ የተሟላ ቁመና ላይ ለመድረስ አሁንም የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉ:: ምክንያቱም ጦርነቱ መሬት ለማስለቀቅ ብቻ ሊሆን አይችልም:: በዋናነት እነዚህን አስቸጋሪ ጣቶች የሚያንቀሳቅሱ ጭንቅላቶች መቆረጥ አለባቸው::

- በጣም አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ፀረ ማጥቃት የምንመለስበት ሁኔታ : ትግራይ በተሟላ አስተማማኝ በተባለ ደረጃ ነፃ አውጥተን ቀጣይ ፓለቲካዊ እጣ ፈንታ ለመውሰድ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር በሚያስችለን ደረጃ ዝግጅታችን አጠናክረናል::

Report Page