*/

*/

Source

* ፊታውራሪ አባ ውርጂ.... በበአምባላጌ ውጊያ ላይ

የአድዋው ጦርነት ከመካሄዱ ጥቂት ወራቶች ቀደም ብሎ አምባላጌ ተራራ (አምባ) ላይ የመሸገውን የጠላትን ጠቅላላ የጦር አቋምና አደረጃጀት ለመገመት እንዲቻል በፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራው የሚመራ 1200 የሚደርስ ግብረ ኃይል የአምባላጌን ዙሪያ መርምሮ እንዲመለስ ታዘዘ።

ጦርነት ግን እንዳይገጥም ተከልክሎ ነበር። ኅዳር 29 ቀን 1888 ዓ.ም ሊነጋጋ ሲል ግብረ ኃይሉ ተንቀሳቅሶ ከአምባው ተጠጋ። የዚያን ጊዜ ከጣልያን ቃፊሮች ጋር ተገናኘ እና ተኩስ ተለዋወጡ። በሙሉ አምባው ላይ የነበረው የጣልያን ጦር ለውጊያ ተንቀሳቀሰ። የገበየሁ ጦር አምባውን ለመውጣት በሚሞክርበት ጊዜ የጣልያን ጦር ከላይ ወደ ታች ያጠቃ ጀመር።

የኢትዮጵያ ወታደር ከፊት ያለው ጓደኛው ሲወድቅ እራሱም እስኪወድቅ ድረስ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አላለም። ሁኔታው ሲታይ የፊት መንገድ ብቻ እንጂ የኋላ መንገድ የሌለ ነበር የመሰለው። በእንዲህ አይነት ሁኔታ ኢትዮጵያውያኑ ከአምባው አናት ደርሰው የጨበጣ ውጊያ ጀመሩ። በዚህም ደህና እየቀናቸው ሄደ።

የጠላት ጦር መሪ የነበረው ማጆር ቶዜሊ ከወዲህ ከወዲያ እየተዘዋወረ በሚያዋጋበት ጊዜ ድንገት ፊታውራሪ አባ ውርጂ ከሚባል የራስ መኮንን ሰው ጋር ተገናኘ። ሽጉጡን እስኪያወጣ ድረስ አባ ውርጂ ጊዜ አልሰጠውም። ትግል ገጥመው ተያይዘው ገደል ገቡ እና የሁለቱም የሕይወት ፍፃሜ ሆነ። በዚህ ምክንያት እንዲህ ተብሎ ተገጠመ

ጀኔራል ባህር ማጆር ቶዞሊ ማን ይነካዋል ያለ ፈጣሪ

ገደል ሰደደው ውርጂ ፊታውራሪ።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_125
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

Report Page