*/

*/

Source
Technology and Innovation Institute, Ethiopia
ሶስት ፀሐይ ያላት ያልተለመደች ፕላኔት
************************ ለሰው ልጆች በተፈጥሮ የተሰጠቸው ፀሐይ በብዙ ነገሯ የተስማማችና ለአዕምሯችንም የተለመደች ናት፡፡ ይሁን እንጂ በስርዓተ ጸሐይ ውስጥ ብዙ ያልተለመዱና አስደናቂ ነገሮች በምርምርና በፍለጋ ሲገኙ መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ በሚልኪ ዌይ ጋላክሲ ውስጥ ያሉ ከዋክብት ቢያንስ አንድ ደባል ኮከብ አላቸው ሲሆን 1800 የብርሃን ዓመት በሚርቀው የዚህ ስርዓተ ፀሐይ ውስጥ በሶስት ከዋክብት ዑደት ውስጥ ያለ ግዙፍ በጋዝ የተሞላ ፕላኔት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ KOI-5 የተባለ የስርዓተ ፀሐይ ክፍል ሲግነስ በሚባለው ስብስብ አካባቢ የተገኘ ሲሆን ኬፕለር በሚባለው የፕላኔቶች ማሰሻ ቴሌስኮፕ አማካኝነት የተገኘ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ በዘርፉ በሚደረገው ምርምር ቁጥራቸው እጅግ ብዙ (4,300) የሆኑ ለተጨማሪ ጥናት የታጩ ግኝቶች (ኤግዞ ፕላኔት) ቢኖሩም ይህ የአሁኑ ግኝት ግን በስርዓተ ፀሐይ ውስጥ እስካሁን ከተገኙት 10 በመቶ የሚሆኑ ባለ ብዙ ፀሐይ (multi-star systems) መካከል የሚመደብ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስለ መልቲ ስታር ኤግዞ ፕላኔት የታወቀው በጣም ጥቂት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አልሸሸጉም፡፡ ምርምሩ መነሻውን ኬፕለር ስራ ከጀመረበት ከ2009 ያደረገ ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ ፍንጮች ሲገኙ ቆይተዋል፡፡ ከግኝቶቹም መካከል KOI-5Ab KOI-5B እና KOI-5C እየተባሉ የሚጠሩትን ማንሳት ይቻላል፡፡ በ2018 ስራውን ከኬፕለር የተረከበው TESS ትኩረቱን ወደ ሲግነስ ስብስብ አደረገ፡፡ በዚህም KOI-5A አካባቢ የሚዞር ትሪፕል ስታር ሲስተም ያለው ፕላኔት መኖሩን አረጋግጧል፡፡ ከዚህ በፊት ትሪፕል ስታር ሲስተም ያላቸው ፕላኔቶች ባይታወቁም ይኛውን የበለጠ የተለየ የሚያደርገው ጥምዝ ምህዋር ያለው መሆኑ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ KOI-5Ab, KOI-5A መድረስ ከተቻለ ሙሉ ስርዓተ ፀሐይን መቆጣጠር ይቻላል ብለው ያስባሉ፡፡ ሳተርን ላይ ሆኖ KOI-5Bን ቢመለከቱት የፀሐይ አይነት እይታ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡ የግኝቱም ውጤት ይፋ የሆነው በ237ኛው የአሜሪካ ስነ-ፈለክ ማህበረሰብ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

ምንጭ Science alert

5 hours ago · Public · in Timeline PhotosView Full Size

Report Page