እልፍብልፍብፍል

እልፍብልፍብፍል

💡dii alex
ዋውውው


ኖኒሽ ቢራቢሮ

የመንገደኛዋ ደብዳቤዎች

...................................

ሌ ላ ፡ ቀ ን ፡ ሆ ነ! ብ ዙ ፡ ሌ ላ ፡ ቀ ና ት ፡ እ ን ዳ ለ ፉ ፡ ሁ ሉ ፡ ይ ሄ ኛ ው ም ፡ እ ን ደ ሚ ያ ል ፍ ፡ አ ዉ ቃ ለ ሁ። ቀ ና ቱ ፡ እ ን ደ ኔ ፡ መ ን ገ ደ ኛ ፡ ይ መ ስ ሉ ኛ ል ፡ መ ድ ረ ሻ የ ን ፡ ሳ ላ ዉ ቅ ፡ እንደምጓዝበት የሀሳብ ጎዳና እነሱም ማለቂያ ወደሌለው ነገ የሚፈረጥጡ........ በእነዚያ ነገ ላይ ለመድረስ ተጣድፈው ባለፉት ቀናት ዉስጥ ከአይኖቼ በብዙ ራቅህ.... ስትርቅ ሽሽትህ ድንገት እንዳልነበረ ይልቁንም መራቅህን ፈልገኸዉ እንደሆነ ደመነፍሴ ሹክ አለኝ፡ ለሹክሹክታዉ ምላሽ ነፈግሁት። ይሂድ የራሱ ጉዳይ! አላልኩም...ለምን መሄድ አሰኘው? ብየም አልጠየቅኩም፡ ዝም አልኩ! ዝምታየ ሲበረታ ስለመራቅህ ያንሾካሾከልኝ ስሜቴም እንደተቆጡት ድንጉጥ ህፃን አኩርፎ ዝም አለ፡ ልቤና ደመነፍሴ ይጋጩ ዘንድ አልወደድኩማ!

ያኔ ምስልህ እየደበዘዘ ሄደ....ለቀናት ከሀሳቤ ሸሸህና የጠፋህ መሰለኝ እናስ ልረሳህ ፈለግኩ እንዴ? አያይይ... ልቤ እንደዛ አይሻም፡ ትናንትን መርሳት ደስ አይለኝም! ትናንትን ከነ ኮተቱ እወደዋለሁ። ስለዚህ ሰበብ ፈጥሬ በትናንትናየ ዉስጥ እፈልግህ ጀመር። ስለ ብዙዎቹ መንገደኛ ትናንቶች ሳስብ ፊት ለፊቴ ተቀምጠዉ በአርስቶትል ሁለት መስመር አባባል ለሁለት ሰአታት ሲከራከሩ ከቆዩት ጓደኞቼ አንዱ አብሬያቸው መኖሬ እንዲታወቀኝ ይመስል ብርጭቆየ ዉስጥ በቀረችዉ ግማሽ አልኮል ላይ በረዶ ጨመረባት ፈገግ ብየ አስተዋልኩት፡

ፈገግታዬ እያልገባዉ እንኳ ለቅፅበት እይታዬን በአይኖቹ መልሶልኝ ወደ ክርክሩ ተመለሰ................. አይኖቹን ከኔ ሲመልስ ተቻኩዬ ያጋመስኩትን ብርጭቆየን አነሳሁና በደምብ ተጎነጨሁለት፡ ከአልኮሉ ይልቅ በረዶው ያደነዘዘኝ መሰለኝ።

ታዲያ በድንዛዜየ መሀል ለምን ትዝ አልከኝ? ለምን በበረዶ ዉስጥ ፈለግኩህ? ደጋግመህ እንደነገርከኝ እንደ በረዶ የቀዘቀዘ ልብ ስላለህ አይደለም.......... ይልቅስ መንገደኛው ሀሳቤ ዉስጥ ላስገባህ ስለፈለግኩ ብቻ ነበር። ሰበብ እየፈለግኩልህ ! ....... ብርጭቆዬ ዉስጥ ተጨማሪ አልኮል ቀዳሁና ከበረዶዉ ጋር እያጫወትኩት ብዙ ቆየሁ ዙሪያየን የተቀመጡት ጓደኞቼ ከሀሳቤና ከብርጭቆዬ ጋር ከነ ነፃነቴ ትተዉኝ የራሳቸውን ደስታ እያጣጣሙ ነበር........ በረዶዉ ሟሙቶ ሲጠፋ ብርጭቆዬን አንስቼ በአንድ ትንፋሽ አጣጣምኩትና ወደ ደረቴ ዝቅ ብዬ "እስኪ አሁን በየት በኩል ወጥተህ እንደምታመልጥ እናያለን" ብየ አንሾካሾኩለት በብዥታየ መካከል ከራሴ ጋር ፈገግ አልኩ ። ቀስ እያለ የሰዉነቴ ሙቀት ሲጨምር ተነህ ራስህን ነፃ ለማዉጣት እየታገልከኝ መሆኑ ገባኝ የደረብኩትን ሹራብ አዉልቄ ወገቤ ላይ አሰርኩትና በነፃነት ነፍሰህ እንድትሄድ ለቀቅኩህ...........በነፋስ አሳብቤ እንደገና ላስብህ አልቻልኩም። የአርስቶትል ደቀመዛሙርት ሆነዉ የዋሉት ወዳጆቼ ባለመስማማት ተስማምተዉ ክርክራቸዉን ቋጭተዉ ነበር። ቤት እንድንቀይር ሲጠይቁኝ ደስ እንዳላችሁ በሚል ምላሽ ትከሻየን ሰብቄ ተነሳሁና ደንገዝገዝ ባለዉ ምሽት ከርቀት የደበዘዘ ብርሀን የሚረጩ አምፖሎች ወደበዙበት የምሽት ክለብ መጓዝ ጀመርን፡ እየቀረብን ስንሄድ በዉል ከማይሰማዉ ሙዚቃ ጋር ልቤ እየደለቀ ነበር........... ከሀሳቤ ርቀህ እየነፈስክ ስትሄድ በብዥታየ መካከል እየተጓዝክ........ እየተጓዝክ እየጠፋህ.....እየጠፋህ.... ስትሄድ ይታወቀኛል። ከሰአታት በዃላ የሌሊቱ አጋማሽ ላይ ደብዘዝ ባለዉ ብርሀን ዉስጥ ከነፍሴ ሙዚቃ ጋር እየተወዛወዝኩ ነዉ።

ነገን ላየዉ እጓጓለሁ

በል ሂድ ዛሬ ጠግቤያለሁ

ከእንግዲህ መቼም ላትመጣ ደህና ሁን በል ሌላ መጣ.............. አንድ ዉብ አበባ ብቻ ማየት አልፈልግም በሀሳቤ ዉስጥ እንዳሻህ ከተመላለስክ በዃላ ስትሄድ ለሌላኛዉ ዉበት ማሰላሰያ የራሴን ነፃነት አወጅኩ! እንደቢራቢሮዋ ሁሌም ዉብ የሆነዉን ሁሉ እፈልጋለሁ እሱም ላይ በነፃነት አርፋለሁ የናፈቅከኝ ለታ በነፈስክበት አቅጣጫ እየተንሳፈፍኩ አስተዉልሀለሁ። እናማ ባለ ግሩም መአዛዉ ወዳጀ ሆይ ዝም ብለህ ንፈስ ነፍሴ በአርምሞ ታደምጥሀለችና.........

ያንተዉ ቢ_ራ_ቢ_ሮ

ሀሙስ ታህሳስ 11/2011

አርባምንጭ_ኢትዮጵያ

Report Page