*/
Sourceየተዛቡ ታሪኮችን የማስተካከል ተልዕኮ(2.3) < ስሜት >
...
አያቴ ሰሚ ያጣ ወጓን ለ'ኔ ትለፍፍልኛለች ። ከነ ሰዋዊ መልኩ ከኩሸቱም ፥ ከቧልቱም ፥ ከእዉነቱም ።
. .
.
... መቼም እንዲያም ፥ እንዲህም እያልን ከጃን ሆይ ጋር ቀጠልን ። በመሀል ያ ሶላቶ ጣልያን ወዲህ ሊመጣ እየገሰገሰ ነዉ ተባለ ። መሳፍንቱ ሁሉ ተረባበሸ፡፡ ዛድያ ንጉሱ ተነስተዉ ህዝቡንም አንቅተዉ ይመክታሉ ብለን ስንጠብቅ 'እኔ እዉጭ ሆኜ ድምጤን ባሰማ ይሻላል' አሉ ።
ይሄኔ ግልፍ ብሎኝ 'ድምጥ ለማሰማት ደሞ አንድ ሁለት አዝማሪ ቢልኩ አይበቃም ወይ? እንዴት አንድ መሪ ህዝቡን ለወራሪዉ ትቶት ይጠፋል? ...' ብዬ ጮህኩ ።
- '' እንዴ ንጉሱ ለይ ነዉ የጮህሽዉ?! '' ፥ ገርሞኝ ጠየቅኩ ፡፡
... '' መልሳቸዉ ከጥያቄዬ በላይ ይገርማል ፡፡ ... ' አንቺ ቡኒ ጭገር ፥ እኛ ካንቺ የተሻለ እንደምናዉቅ አታዉቂምን?' ነበር ያሉኝ ፡፡ ... ሰዉ በወጉ 'ፈራሁ' ይላል እንጂ የተወረረች ሀገርን ጥሎ እየሄደ ለምን ሲሉት 'ልለፍፍን' እንደምክንያት ያቀርባል ወይ? ድምጥ ማሰማቱም ይሁን ግድ የለም ። ግን ዲስኩርን ለማቀበል የእሳቸዉ መሄድ እሳቸዉ ባሉት ልክ አስፈላጊ ነበር?
አየህ ፥ ቀሚስህን ስትገልብለት የኖርከዉ ሰዉዬን ማንነት በድንገት ተገልጦ እንደማየት ያለ መቅሰፍት የለም ። ወላ ከቀሚሴ ቆርጬ ለእሳቸውም ላሰፋላቸዉ ነበር ፥ መቼም የመጨረሻ አቅማቸዉ ማዉራት ከሆነ እንደዘመኗ ሴት ማጀት ይግቡ እንጂ ዙፋን ለይ ምን ይሰራሉ?
የሆነዉ ሆነና ጣሊያን ሲመጣ እሳቸዉ ሸሹ ። አርበኛዉም መሳሪዉን እየወደረ ሸፈተ ። ብዙም ሳይቆይ ጣሊያን አቡነ ጴጥሮስን እየፈለጋቸዉ ነዉ ተብሎ ተነዛ ። ይሄኔ ሰዉ አስልኬ በስንት ልመና እኔ ጋር እንዲሸሸጉ አረግኩ ። መቸም በዉሽምነቴ ቢንቁኝም ፥ ሲዘረጋ ቀዬዉን በሚያካልለዉ ዘርፋፋዉ ቀሚሴ ሳያከብሩኝ አልቀሩም ። በዚህም ትንሽ ተግባባን ። ዛድያ የዚያ የጥልያን ጆሮ ጠቢዉ በዝቶ ኖሮ እኔ ቤት እንዳረፉ ይሰሙና ሊወስዱብኝ ሲገሰግሱ ይመጣሉ ፡፡ ሲደርሱ ከእልፍኝ አስከልካዮቹ ጋር በልግባ አትገባም መረባበሽ ይሆናል ።
... ይህኔ አቡኑን ወየት ልሸሽጋቸዉ? ቢቸግረኝ ለዘርፋፋዉን ቀሚሴ ቅድ አበጅቼ ፥ እሷንም ገለብ አድርጌ እንዲሸሸጉ ጠየቅኳቸዉ ። እሳቸዉ ግን በፍጡም አሉ ፡፡ አረ ተዉ ሞትና ኩራት አይገጥምም አርፈዉ ይሸሸጉ አልኳቸዉ ፥ እሳቸዉ ግን ፈገግ እንዳሉ 'ከቀሚስሽ ዘልቄ ከዚያ ከማላገኘዉ ሻንቅላሽ ጋር ከምፋጠጥስ እንዲሁ ብሞት እመርጣለሁ ' አሉኝ ።
መቼም አብዛኛዎቻችን በክብር የተጀበኖ ስሜትን ለማጤን የምትሆን ንቃት የለችንም ፡፡ ... ከካባ ባሻገር ፥ ከቆብ ወዲያ ስላለ ነዲድ ስሜት ለማገናዘብ እንቦዝናለ፡፡ አየህ ፥ ያን ቀን አይናቸዉ ዉስጥ ያየሁትን ስምና ክብር የጠፈረዉ ስሜትና መጠማት እስካሁን ዉል ይልብኛል ።
... ነዲድ የብድ ስሜትን ታቃፊ ሆኖ ተፈጥሮ ሳይበዱ መኖር እንዴት ያለ ፍርጃ ነዉ?... አየህ ፥ ነብስ እንድትነፃ ስጋን መጨቆን የሁል ግዜ መፍትሔ አይሆንም ።አቡነዘበሰማያትን እየደገምን የጭን ጥማችንን እንድናስብ የሚያደርገን ከማግኘት ይልቅ ማጣት አይደለም? ሰዉን ከተፈጥሮዉ ማናጠብ ከራሱ ማድረግ ነዉ ።
አየህ አቡኑ ወጣት ነበሩ ፥ እሳቱን ከዉሀዉ የሚሉ ። የዕድሜ ፍላታቸዉን የሚያስረሳ ማዕረግም አላቸዉ ። ዛድያ ማን አየላቸዉ መብዳት ያምራቸዉ እንደሆን? ሰዉ የተፈጠረዉ ሰዉ እንዲሆን እንጂ ለመልዓክትነት እንዲንጠራራ አይደለም ። ሰዉ መሆን ደሞ ለሰዉኛ ስሜቶች ፈር ባለዉ መልኩ መታዘዝንም ያዳብላል፡፡ ... መቸም ዋልድባ ስለገባህ ፥ ቁላህ ቀድሞ መንቃቱን አያቆምም አይደል?
... እኔ አሁን እንኳ ሰዉ ስለ አቡኑ ሲወራ ትዝ የሚለኝ መረሸናቸዉ አይደለም ፥ ሳላቀምሳቸዉ መሞታቸዉ ነዉ ። ሞትማ ለሁሉም አለ አይደል?